ዘኍል 14:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 ከርስታቸው እነርሱን ለማጥፋት በቸነፈር እመታቸዋለሁ፤ አንተንም ከእነርሱ ይልቅ ታላቅና ኃያል የሆነ ሕዝብ አደርግሃለሁ።” See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 በቸነፈር እመታዋለሁ፤ እደመስሰዋለሁም፤ አንተን ግን ብርቱና ታላቅ ለሆነ ሕዝብ አደርግሃለሁ።” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 እነሆ፥ እኔ ቸነፈር አምጥቼ በመቅሠፍት እደመስሳቸዋለሁ፤ አንተን ግን ከእነርሱ ይበልጥ ታላቅና ብርቱ ለሆነ ሕዝብ አባት አደርግሃለሁ።” See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 በሞት እቀጣቸዋለሁ፤ አጠፋቸዋለሁም፤ አንተንና የአባትህን ቤት ግን ለታላቅና ከዚህ ለሚበዛ ሕዝብ አደርግሃለሁ” አለው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 ከርስታቸው አጠፋቸው ዘንድ በቸነፈር እመታቸዋለሁ፤ አንተንም ከእነርሱ ለሚበዛና ለሚጠነክር ሕዝብ አደርግሃለሁ አለው። See the chapter |