Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 13:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ወደ ኤሽኮልም ሸለቆ መጡ፥ ከዚያም ከወይኑ አንድ ሙሉ ዘለላ የነበረበትን አረግ ቈረጡ፥ ከእነርሱም ሁለት ሰዎች በመሎጊያ ተሸከሙት፤ ደግሞም ከሮማኑ ከበለሱም አመጡ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ወደ ኤሽኮል ሸለቆ በደረሱ ጊዜ የወይን ዘለላ ያንዠረገገ አንድ ቅርንጫፍ ቈረጡ፤ ይህንም ከሮማንና ከበለስ ጋራ በመሎጊያ አድርገው ለሁለት ተሸከሙት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 አልፈውም ወደ ኤሾኮል ሸለቆ ደረሱ፤ ከዚያም የወይን ዘለላ ያለበትን ቅርንጫፍ ቈረጡ፤ ያንንም የወይን ዘለላ አንድ ሰው ብቻውን ሊሸከመው የማይችል ከባድ ከመሆኑ የተነሣ ሁለት ሰዎች በመሎጊያ በትከሻቸው ላይ ተሸከሙት፤ ከዚህም ጋር የሮማንና የበለስ ፍሬ ይዘው መጡ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ወደ ወይን ዘለላ ሸለ​ቆም መጡ፤ አዩ​ኣ​ትም፤ ከዚ​ያም ከወ​ይኑ አንድ ዘለላ የነ​በ​ረ​በ​ትን አረግ ቈረጡ፤ በመ​ሎ​ጊ​ያም ተሸ​ከ​ሙት፤ ደግ​ሞም ከሮ​ማኑ ከበ​ለ​ሱም አመጡ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ወደ ኤሽኮልም ሸለቆ መጡ፥ ከዚያም ከወይኑ አንድ ዘለላ የነበረበትን አረግ ቈረጡ፥ ሁለቱም ሰዎች በመሎጊያ ተሸከሙት፤ ደግሞም ከሮማኑ ከበለሱም አመጡ።

See the chapter Copy




ዘኍል 13:23
6 Cross References  

ወደ ኤሽኮልም ሸለቆ ሄደው ምድሪቱን ባዩ ጊዜ፥ ጌታ ወደ ሰጣቸው ምድር እንዳይገቡ የእስራኤልን ልጆች ልብ አደከሙ።


የእስራኤል ልጆች ከዚያ ስለ ቈረጡት ዘለላ የዚያን ስፍራ ስም የኤሽኮል ሸለቆ ብለው ጠሩት።


ከጊዜ በኋላ ሳምሶን በሶሬቅ ሸለቆ የምትኖር ደሊላ የምትባል አንዲት ሴት ወደደ።


አንድ የሸሸ ሰውም መጣ፥ ለዕብራዊው ለአብራምም ነገረው፥ እርሱም የኤስኮል ወንድምና የአውናን ወንድም በሆነ በአሞራዊ መምሬ የባሉጥ ዛፎች አጠገብ ይኖር ነበር፥ እነዚያም ከአብራም ጋር ቃል ኪዳን ገብተው ነበር።


የስንዴና ገብስ፥ የወይንና በለስ ዛፍ እንዲሁም ሮማን፥ የወይራ ዛፍና ማር ወደ ሞሉባት ምድር፥


Follow us:

Advertisements


Advertisements