Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘኍል 1:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በሁለተኛውም ወር በመጀመሪያው ቀን ማኅበሩን ሁሉ ሰብሰቡአቸው፤ እነርሱም ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለውን አንድ በአንድ እንደየስማቸው ቍጥር፥ በየወገኖቻቸው በየአባቶቻቸውም ቤቶች ትውልዳቸውን መዘገቡ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ከዚያም በሁለተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ማኅበረ ሰቡን በሙሉ በአንድነት ሰበሰቧቸው። የተሰበሰቡትም በየጐሣቸውና በየቤተ ሰባቸው የትውልድ ሐረጋቸውን ተናገሩ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ሁለተኛው ወር በገባ በመጀመሪያው ቀን፥ ማኅበሩን ሁሉ በአንድነት ሰብስበው በየነገዱና በየቤተሰቡ ከመደቡ በኋላ የሕዝብ ቈጠራ አደረጉ፤ ዕድሜአቸው ኻያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት ስማቸው እየተመዘገበ ተቈጠሩ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 በሁ​ለ​ተ​ኛው ዓመት በሁ​ለ​ተ​ኛ​ውም ወር በመ​ጀ​መ​ሪ​ያው ቀን ማኅ​በ​ሩን ሁሉ ሰበ​ሰ​ቡ​አ​ቸው፤ ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚ​ያም በላይ ያለ​ውን ወንድ ሁሉ በየ​ራሱ፥ በየ​ወ​ገ​ኑም፥ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም ቤቶች፥ በየ​ስ​ማ​ቸው ቍጥር ትው​ል​ዳ​ቸ​ውን ተና​ገሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 በሁለተኛውም ወር በመጀመሪያው ቀን ማኅበሩን ሁሉ ሰብሰቡአቸው፤ ከሀያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያለውን በየራሱ በየወገኑም በየአባቶቻቸውም ቤቶች በየስማቸው ቍጥር ትውልዳቸውን ተናገሩ።

See the chapter Copy




ዘኍል 1:18
7 Cross References  

ከቴልሜላሕ፥ ቴልሐርሻ፥ ክሩብ፥ ዓዳን፥ ኢሜር የወጡ እነዚህ ነበሩ፤ ነገር ግን የአባቶቻቸውን ቤቶችና ዘራቸውን ወይም ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ማስታወቅ አልቻሉም፤


አባትና እናት የትውልድም ሐረግም የሉትም፤ ለዘመኑም መጀመሪያ ለሕይወቱም ፍጻሜ የለውም፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ልጅ ተመስሎ ለዘላለም ካህን ሆኖ ይኖራል።


ከቴልሜላሕ፥ ከቴል ሀርሻ፥ ከክሩብ፥ ከአዶንና ከኢሜር የወጡ እነዚህ ናቸው፤ ነገር ግን የአባቶቻቸውን ቤትና ዘራቸውን ወይም ከእስራኤል ወገን መሆናቸውን ማስረዳት አልቻሉም፤


ይህ ሰው ምንም ትውልዱ ከእነርሱ ባይቆጠርም እንኳ ከአብርሃም አሥራትን ተቀብሏል፤ የተስፋ ቃል የተሰጠውን አብርሃምንም ባርኮአል።


ጌታም ሙሴን በሲና ምድረ በዳ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ፥ በሁለተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን፥ ከግብጽ ምድር ከወጡ በኋላ በሁለተኛው ዓመት እንዲህ ብሎ ተናገረው፦


ሙሴና አሮንም እነዚህን በስማቸው ተጠርተው የነበሩትን ሰዎች ወሰዱአቸው፤


የአባቶቻቸው ቤት አለቆች እነዚህ ናቸው። የእስራኤል የበኩር ልጅ የሮቤል ልጆች ሐኖክ፥ ፋሉ፥ ሔፅሮንና ካርሚ፤ እነዚህ የሮቤል ወገኖች ናቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements