Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ነህምያ 9:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 አብራምን የመረጥህ፥ ከከለዳውያን ኡር የአወጣኸው፥ ስሙንም አብርሃም ያልኸው፥ አንተ ጌታ አምላክ ነህ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “አብራምን የመረጥኸውና ከከለዳውያን ዑር አውጥተህ አብርሃም የሚል ስም የሰጠኸው አንተ እግዚአብሔር አምላክ ነህ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 የባቢሎን ክፍል ከሆነችው ዑር፥ አብራምን መርጠህ ያመጣኸው፥ ስሙንም አብርሃም ያልከው፥ አንተ እግዚአብሔር አምላክ ነህ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 አንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ነህ፤ አብ​ራ​ምን መረ​ጥህ፤ ከዑር ከላ​ው​ዴ​ዎ​ንም አወ​ጣ​ኸው፤ ስሙ​ንም አብ​ር​ሃም አል​ኸው፤

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 አንተ እግዚአብሔር አምላክ ነህ፥ አብራምን መረጥህ፥ ከዑር ከላውዴዎንም አወጣኸው፥ ስሙንም አብርሃም አልኸው፥

See the chapter Copy




ነህምያ 9:7
11 Cross References  

ከዛሬም ጀምሮ እንግዲህ ስምህ አብራም ተብሎ አይጠራ፥ ነገር ግን ስምህ አብርሃም ይሆናል፥ ለብዙ አሕዛብ አባት አድርጌሃለሁና።


ታራም ልጁን አብራምን፥ የልጅ ልጁን የሐራንን ልጅ ሎጥንና የልጁንም የአብራምን ሚስት ምራቱን ሣራን ወሰደ፥ ከእርሱም ጋር ወደ ከነዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከለዳውያን ዑር ወጡ፥ ወደ ካራንም መጡ፥ ከዚያም ተቀመጡ።


ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃም፥ ወደ ወለደቻችሁም ወደ ሳራ ተመልከቱ፤ አንድ ብቻውን በሆነ ጊዜ ጠራሁት፥ ባረክሁትም አበዛሁትም።


ብቻ ጌታ ስለ አባቶችህ ደስ ብሎታል፥ እነርሱንም ወድዶአል፥ ከእነርሱም በኋላ እናንተን ዘራቸውን እንደ ዛሬው ሁሉ ከአሕዛብ ሁሉ መካከል መረጠ።


ይህችን ምድር ትወርሳት ዘንድ እንድሰጥህ ከከለዳውያን ዑር ያወጣሁህ እግዚአሔር እኔ ነኝ አለው።


ጽድቅንና ፍርድን በማድረግ የእግዚአብሔርን መንገድ ይጠብቁ ዘንድ ልጆቹንና ከእርሱ በኋላ ቤቱን እንዲያዝዝ አውቃለሁና፥” ይህም እግዚአብሔር በአብርሃም ላይ የተናገረውን ነገር ሁሉ ያመጣ ዘንድ ነው።


አብርሃም የተባለ አብራም።


Follow us:

Advertisements


Advertisements