ነህምያ 8:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 ሕዝቡም ሁሉ ሊበሉ፥ ሊጠጡ፥ ለሌላቸው ድርሻቸውን ሊልኩና ታላቅ ደስታ ሊያደርጉ ሄዱ፤ የተነገራቸውን ቃል ማስተዋል ችለው ነበርና። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 ስለዚህ ሕዝቡ ሁሉ የተነገራቸውን ቃል ተረድተው ስለ ነበረ፣ ለመብላት፣ ለመጠጣት፣ ከምግባቸው ከፍለው ለመላክና ሐሤትም ለማድረግ ሄዱ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 የተነበበላቸውን ቃል ትርጒም በሚገባ ተረድተው ስለ ነበር ሕዝቡ ሁሉ ወደየቤታቸው ሄደው በመብላትና በመጠጣት እጅግ ተደሰቱ፤ ያላቸውንም ምግብ ከሌሎቹ ጋር አብረው ተካፈሉ፤ See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 ሕዝቡም ሁሉ የተነገራቸውን ቃል አስተውለዋልና ሊበሉና ሊጠጡ፥ እድል ፈንታም ሊልኩ፥ ደስታም ሊያደርጉ ሄዱ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 ሕዝቡም ሁሉ የተነገረላቸውን ቃል አስተውለዋልና ሊበሉና ሊጠጡ እድል ፈንታም ሊሰድዱ ደስታም ሊያደርጉ ሄዱ። See the chapter |