Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ነህምያ 7:72 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

72 ካህናቱ፥ ሌዋውያኑ፥ በር ጠባቂዎቹ፥ መዘምራኑ፥ ከሕዝቡ አንዳንዶቹ፥ የቤተ መቅደስ አገልጋዮችና እስራኤልም ሁሉ በገዛ ከተሞቻቸው ተቀመጡ፥ ሰባተኛውም ወር መጣ የእስራኤል ልጆችም በገዛ ከተሞቻቸው ተቀምጠው ነበር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

72 የቀረው ሕዝብ በአጠቃላይ የሰጠው 20,000 የወርቅ ዳሪክ 2,000 ምናን ብርና 67 ልብሰ ተክህኖ ነበር።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

72 የቀ​ሩ​ትም ሕዝብ የሰ​ጡት ሃያ ሺህ የወ​ርቅ ዳሪ​ክና ሁለት ሺህ ምናን ብር፥ ስድሳ ሰባ​ትም የካ​ህ​ናት ልብስ ነበረ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

72 የቀሩትም ሕዝብ የሰጡት ሀያ ሺህ የወርቅ ዳሪክና ሁለት ሺህ ምናን ብር፥ ስድሳ ሰባትም የካህናት ልብስ ነበረ።

See the chapter Copy




ነህምያ 7:72
5 Cross References  

የቀሩት ሕዝብ የሰጡት ሀያ ሺህ የወርቅ ዳሪክና ሁለት ሺህ ምናን ብርና ስድሳ ሰባት የካህናት ልብስ ነበረ።


ሒልቂያ፥ አሒቃም፥ ዐክቦር፥ ሳፋንና ዐሣያ በኢየሩሳሌም አዲስ በተሠራው ሰፈር የምትኖረውን ሑልዳ ተብላ የምትጠራውን ነቢይት ለመጠየቅ ሄዱ፤ የሐርሐስ የልጅ ልጅ የቲቅዋ ልጅ የሆነው ባሏ ሻሉም የቤተ መቅደስ አልባሳት ኃላፊ ነበር፤ እነርሱም የሆነውን ሁሉ ለነቢይቱ አስረዱአት።


ሰባተኛውም ወር በደረሰ ጊዜ፥ የእስራኤልም ልጆች በከተሞች ነበሩ፥ ሕዝቡ እንደ አንድ ሰው ሆነው ወደ ኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ።


ማሉክ፥ ሐሪም፥ ባዓና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements