ነህምያ 3:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)30 ከእርሱ በኋላ የሼሌምያ ልጅ ሐናንያና የጻላፍ ስድስተኛው ልጁ ሐኑን ሌላውን ክፍል አደሱ። ከእርሱ በኋላ የቤሬክያ ልጅ ሜሹላም ከክፍሉ ፊት ለፊት ያለውን አደሰ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም30 ከርሱ ቀጥሎ ያለውን ሌላ ክፍል ደግሞ የሰሌምያ ልጅ ሐናንያና የሴሌፍ ስድስተኛ ልጅ ሐኖን መልሰው ሠሩ። ከእነርሱም ቀጥሎ የቤራክያ ልጅ ሜሱላም ከመኖሪያው ትይዩ ያለውን መልሶ ሠራ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም30 የሼሌምያ ልጅ ሐናንያና የጻላፍ ስድስተኛ ልጅ ሐኑን ለሁለተኛ ጊዜ የተሰጣቸውን ድርሻ ሠሩ። የበራክያ ልጅ መሹላምም በመኖሪያ ቤቱ ፊት ለፊት በኩል ያለውን ሠራ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)30 ከእርሱም በኋላ የሰሎምያ ልጅ ሐናንያና የሴሌፍ ስድስተኛው ልጁ ሐኖን ሌላውን ክፍል ሠሩ። ከዚያም በኋላ የበራክያ ልጅ ሜሱላም በሙዳየ ምጽዋቱ አንጻር ያለውን ሠራ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)30 ከእርሱ በኋላ የሰሌምያ ልጅ ሐናንያና የሴሌፍ ስድስተኛው ልጁ ሐኖን ሌላውን ክፍል አደሱ። ከዚያም በኋላ የበራክያ ልጅ ሜሱላም በጓዳው አንጻር ያለውን አደሰ። See the chapter |