Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ነህምያ 13:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 በውኑ ይህን ሁሉ ታላቅ ክፋት እንሠራ፥ እንግዶችንም ሴቶች በማግባት አምላካችንን እንበድል ዘንድ እናንተን እንስማ?

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 እናንተም ደግሞ ባዕዳን ሴቶችን በማግባት ይህን የመሰለ ታላቅ በደል እንደምትፈጽሙና ለአምላካችንም ታማኞች እንዳልሆናችሁ መስማት ይገባናልን?”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ታዲያ እኛስ የእናንተን ምሳሌነት መከተልና የባዕዳን አገሮች ሴቶችን በማግባት የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መተላለፍ ይገባናልን?”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 እን​ዲሁ እን​ግ​ዲህ ይህን ሁሉ ታላቅ ክፋት ስት​ሠሩ፥ እን​ግ​ዶ​ች​ንም ሴቶች በማ​ግ​ባት አም​ላ​ካ​ች​ንን ስት​በ​ድሉ አን​ስ​ማ​ባ​ችሁ።”

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 በውኑ ይህን ሁሉ ታላቅ ክፋት እንሠራ፥ እንግዶችንም ሴቶች በማግባት አምላካችንን እንበድል ዘንድ እናንተን እንስማ?

See the chapter Copy




ነህምያ 13:27
5 Cross References  

ከዔላም ልጆች ወገን የነበረ፥ የይሒኤል ልጅ ሽካንያ ዕዝራን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ “ለአምላካችን ታማኞች አልሆንም፥ የምድሪቱን ሕዝቦች እንግዶች ሴቶችን አግብተናል፥ አሁንም ግን በዚህ ነገር ለእስራኤል ተስፋ አለ።


የምትሉትን ማን ይቀበላችኋል? ከጓዝ ጋር የቀረው ሰው ድርሻ ለጦርነት ከወጣው ሰው ድርሻ ጋር አይበላለጥም፤ ሁሉም እኩል ይካፈላሉ።”


ደግሞም በዚያ ወራት የአዛጦንና የአሞንን የሞዓብንም ሴቶች ያገቡትን አይሁድ አየሁ።


ትእዛዝህን ለማፍረስ፥ ርኩስ ሥራን ከሚሠሩ ከእነዚህም ሕዝቦች ጋር ለመጋባት እንመለሳለንን? አንተስ ትሩፋን የሌለንና የማናመልጥ እስክንሆን ድረስ እንድታጠፋን አትቆጣምን?


ሴቶች ልጆቻችንን ለምድሪቱ ሕዝቦች አንሰጥም፥ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለወንዶች ልጆቻችን አንወስድም፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements