Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ነህምያ 13:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 በዚያም ቀን የሙሴን መጽሐፍ በሕዝቡ ጆሮ ከፍ ባለ ድምፅ አነበቡ፤ አሞናዊ ወይም ሞዓባዊ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ ለዘለዓለም እንዳይገባ የሚል በዚያ ተጽፎ ተገኘ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በዚያም ቀን የሙሴን መጽሐፍ ከፍ ባለ ድምፅ ለሕዝቡ አነበቡ፤ አሞናዊም ሆነ ሞዓባዊ ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ ፈጽሞ እንዳይገባ የሚከለክል ተጽፎ ተገኘ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የኦሪት ሕግ ከፍ ባለ ድምፅ በተነበበላቸው ጊዜ ሰዎቹ ሲያዳምጡ “ሞአባውያንና ዐሞናውያን ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር ለዘለዓለም አይቀላቀሉ” ከሚለው አንቀጽ ደረሱ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በዚ​ያም ቀን የሙ​ሴን መጽ​ሐፍ በሕ​ዝቡ ጆሮ አነ​በቡ፤ አሞ​ና​ው​ያ​ንና ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጉባኤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዳ​ይ​ገቡ የሚል በዚያ አገኙ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 በዚያም ቀን የሙሴን መጽሐፍ በሕዝቡ ጆሮ አነበቡ፥ አሞናውያንና ሞዓባውያንም ወደ እግዚአብሔር ጉባኤ ለዘላለም እንዳይገቡ የሚል በዚያ ተገኘ።

See the chapter Copy




ነህምያ 13:1
22 Cross References  

በየስፍራቸውም ቆመው የጌታ አምላካቸውን የሕግ መጽሐፍ የቀኑ ሩብ ያህል አነበቡ፥ የቀኑ ሩብ ደግሞ እየተናዘዙና፥ ለጌታ አምላካቸው እየሰገዱ አሳለፉ።


ደግሞም በዚያ ወራት የአዛጦንና የአሞንን የሞዓብንም ሴቶች ያገቡትን አይሁድ አየሁ።


እነርሱም ካህናት፥ ነቢያት፥ ሌሎችም ሰዎች ከታናሾች ጀምሮ እስከ ታላቆች ድረስ ወደ ቤተ መቅደስ መጡ፤ ንጉሡም በዚያ ጠፍቶ በነበረውና በቤተ መቅደስ በተገኘው መጽሐፍ የሰፈረውን ቃል በሙሉ ለሕዝቡ አነበበ፤


ሙሴስ ከቀደሙት ትውልድ ጀምሮ በሰንበት በሰንበት በምኵራቦቹ ሲያነቡ በየከተማው እርሱን የሚሰብኩ አሉት።”


ሕግና ነቢያትም ከተነበቡ በኋላ የምኵራቡ አለቆች “ወንድሞች ሆይ! ሕዝብን የሚመክር ቃል እንዳላችሁ ተናገሩ፤” ብለው ላኩባቸው።


እርሱም፦ “በሕግ ምን ተጽፎአል? እንዴትስ ታነበዋለህ?” አለው።


ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ዳርቻቸውን ለማስፋት ሲሉ የገለዓድን እርጉዞች ቀድደዋልና ስለ ሦስት የአሞን ልጆች ኃጢአት ስለ አራትም መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።


ስለ ሞዓብ፤ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ናባው ጠፍታለችና ወዮላት! ቂርያታይም አፍራለች ተይዛለችም፤ አምባይቱም አፍራለች ፈርሳለችም።


በጌታ መጽሐፍ ፈልጉ አንብቡም፤ የጌታ አፍ አዝዞአልና፥ መንፈሱ ሰብስቦአቸዋልና ከእነዚህ አንዲት አትጠፋም፥ ጥንዱን የሚያጣ የለም።


ወደ አምላካችን ጸለይን፥ በእነርሱም ምክንያት በሌሊትና በቀን በእነሱ ላይ ጠባቂ አቆምን።


ሖሮናዊው ሳንባላጥ፥ አገልጋይ የሆነው አሞናዊው ጦብያና ዓረባዊው ጌሻም ይህንን ሰሙ፤ አፌዙብን፤ አንቋሸሹንም፤ “ይህ የምታደርጉት ነገር ምንድነው? በንጉሡ ላይ እያመፃችሁ ነውን?” አሉ።


ሖሮናዊው ሳንባላጥና አገልጋይ የሆነው አሞናዊው ጦብያ ለእስራኤል ልጆች መልካምን ነገር የሚሻ ሰው እንደመጣ በሰሙ ጊዜ እጅግ ተበሳጩ።


በወንዙ አጠገብ ባለችው በሕዝቡ ልጆች ምድር በፋቱራ የተቀመጠውን የቢዖርን ልጅ በለዓምን እዲጠሩት እንዲህ ብሎ መልእክተኞቹን ላከ፦ “እነሆ፥ ከግብጽ የወጣ ሕዝብ አለ፤ እነሆም፥ የምድሩን ሁሉ ፊት ሸፍኖአል፥ በአቅራቢያችንም ተቀምጦአል።


ካህኑ ዕዝራ በሰባተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ሕጉን ወንዶች፥ ሴቶችና አስተውለው መስማት የሚችሉ ባሉበት በጉባኤው ሁሉ ፊት አመጣው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements