Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ነህምያ 12:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ካህናቱና ሌዋውያኑም ራሳቸውን አነጹ፤ ሕዝቡን፥ በሮቹንና ቅጥሩንም አነጹ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ካህናቱና ሌዋውያኑ በሥርዐቱ መሠረት ራሳቸውን ካነጹ በኋላ፣ ሕዝቡን፣ ቅጥሩንና በሮቹን አነጹ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ካህናቱና ሌዋውያኑም ስለ ሕዝቡ ራሳቸው ስለ ከተማይቱ በሮችና ስለ ቅጽሩ የማንጻትን ሥርየት ፈጸሙ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ካህ​ና​ቱና ሌዋ​ው​ያ​ኑም ራሳ​ቸ​ውን አነጹ፤ ሕዝ​ቡ​ንም፥ በረ​ኞ​ች​ንም ቅጥ​ሩ​ንም አነጹ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ካህናቱና ሌዋውያኑም ራሳቸውን አነጹ፥ ሕዝቡንም በሮቹንም ቅጥሩንም አነጹ።

See the chapter Copy




ነህምያ 12:30
14 Cross References  

የግብዣውም ቀኖች ባለፉ ጊዜ ኢዮብ፦ “ምናልባት ልጆቼ በድለው፥ እግዚአብሔርንም በልባቸው ሰድበው ይሆናል” ብሎ ይልክና ይቀድሳቸው ነበር፥ ኢዮብም ማልዶ ይነሣና እንደ ቁጥራቸውም ሁሉ የሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርብ ነበር። ኢዮብም ሁልጊዜ እንዲህ ያደርግ ነበር።


ከምርኮ የተመለሱት የእስራኤል ልጆች፥ የእስራኤልን አምላክ ጌታን ለመፈለግ ራሳቸውን ከምድር አሕዛብ ርኩሰት ለይተው ወደ እነርሱ መጥተው የነበሩት ሁሉ በሉት።


እንዲህም አላቸው፦ “ሌዋውያን ሆይ! ስሙኝ፤ ተቀደሱ፥ የአባቶቻችሁንም አምላክ የጌታን ቤት ቀድሱ፤ ርኩሱንም ነገር ሁሉ ከመቅደሱ አስወግዱ።


ጌታም ሙሴን አለው፦ “ወደ ሕዝቡ ሂድ፥ ዛሬና ነገን ቀድሳቸው፥ ልብሳቸውንም ይጠቡ፤


በዚህም ምክንያት ስለ ሕዝብ እንደሚያቀርብ እንዲሁ ስለ ራሱ ደግሞ መሥዋዕትን ስለ ኃጢአት ሊያቀርብ ይገባዋል።


ሊቀ ካህናት ሁሉ ስለ ኅጢአት መባንና መሥዋዕትን ሊያቀርብ ከሰው ተመርጦ ለእግዚአብሔር በሆነው ነገር ሁሉ ስለ ሰው ይሾማልና፤


ከእንግዳ ነገርም ሁሉ አነጻኋቸው፥ ለካህናቱና ለሌዋውያኑም እያንዳንዳቸው በየሰሞናቸው፥


ሌዋውያኑንም ራሳቸውን እንዲያነጹ፥ መጥተውም በሮቹን እንዲጠብቁ፥ የሰንበትንም ቀን እንዲቀድሱ ነገርኋቸው። አምላኬ ሆይ፥ ስለዚህ ደግሞ አስበኝ፥ እንደ ምሕረትህም ብዛት ራራልኝ።


ነገር ግን ካህናቱ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለመግፈፍ ጥቂቶች ነበሩ፤ ስለዚህም ሌዋውያን በቅን ልብ ከካህናት ይልቅ ይቀደሱ ነበርና ሥራው እስኪፈጸም ድረስ፥ ካህናቱም እስኪቀደሱ ድረስ ወንድሞቻቸው ሌዋውያን ያግዙአቸው ነበር።


ሕዝቡንም፦ “ለሦስተኛው ቀን ተዘጋጁ፥ ወደ ሴትም አትቅረቡ” አላቸው።


ስለዚህ ያዕቆብ ለቤተሰቡና ከእርሱ ጋር ላሉት ሁሉ እንዲህ አለ፦ “እንግዶቹን አማልክት ከመካከላችሁ አስወግዱ ንጹሐንም ሁኑ፥ ልብሳችሁንም ለውጡ፥


መዘምራኑም በኢየሩሳሌም ዙሪያ መንደሮች ሠርተው ነበርና ከቤትጌልገላም፥ ከጌባና ከዓዝሞት እርሻዎች ተሰበሰቡ።


የእስራኤልንም አምላክ የጌታን ታቦት ለማምጣት ካህናቱና ሌዋውያኑ ተቀደሱ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements