ነህምያ 11:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)30 ዛኖሓ፥ ዓዱላምና በመንደሮቻቸው፥ ላኪሽና ሜዳዎችዋ፥ ዓዚቃና በመንደሮችዋ፤ እንዲሁ ከቤርሳቤህ ጀምሮ እስከ ሄኖም ሸለቆ ድረስ ሰፈሩ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም30 በዛኖዋ፣ በዓዶላምና በመንደሮቻቸው፣ በለኪሶና በዕርሻዎቿ፣ በዓዜቃና በመንደሮቿ። ስለዚህ ከቤርሳቤህ ጀምሮ እስከ ሄኖም ሸለቆ ባለው ስፍራ ሁሉ ተቀመጡ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም30 በዛኖሐ፥ በዐዱላምና በእነዚህም ከተሞች አጠገብ በሚገኙት መንደሮች ሁሉ ይኖሩ ነበር፤ ላኪሽና በአቅራቢያዋ የሚገኙ የእርሻ ቦታዎች፥ ዐዜቃና የአካባቢዋ መንደሮች ሁሉ የእነርሱ መኖሪያዎች ነበሩ፤ በዚህ ዐይነት የይሁዳ ሕዝብ መኖሪያ በደቡብ ከቤርሳቤህ፥ በሰሜን ከሂኖም ሸለቆ በመለስ ባለው ክልል ውስጥ ነበር። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)30 በዛኖህ፥ በዓዶላም፥ በመንደሮቻቸውም፥ በለኪሶና በእርሻዎችዋ፥ በዓዜቃና በመንደሮችዋ ተቀመጡ። እንዲሁ ከቤርሳቤህ ጀምሮ እስከ ሄኖም ሸለቆ ድረስ ሰፈሩ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)30 በጾርዓ፥ በየርሙት፥ በዛኖዋ በዓዶላም በመንደሮቻቸውም፥ በለኪሶና በእርሻዎችዋ፥ በዓዜቃና በመንደሮችዋ ተቀመጡ። እንዲሁ ከቤርሳቤህ ጀምሮ እስከ ሄኖም ሸለቆ ድረስ ሰፈሩ። See the chapter |