ነህምያ 10:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)34 እኛም፥ ካህናቱና ሌዋውያኑ ሕዝቡም፥ እንደ አባቶቻችን ቤቶች በተወሰነ ጊዜ በየዓመቱ ወደ አምላካችን ቤት አምጥተን በሕጉ እንደ ተጻፈ በአምላካችን በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ይቃጠል ዘንድ ስለ እንጨት ቁርባን ዕጣ ተጣጣልን፥ See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም34 “እኛ፣ ማለት ካህናቱ፣ ሌዋውያኑና ሕዝቡ በየዓመቱ በተወሰነው ጊዜ በሕጉ እንደ ተጻፈው፣ በአምላካችን በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ የሚነድደውን ዕንጨት የእያንዳንዳችን ቤተ ሰብ መቼ ወደ አምላካችን ቤት ማምጣት እንዳለበት ለመወሰን ዕጣ ተጣጣልን። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም34 በሕጉ ስለ መሥዋዕት በተጻፈው መሠረት ለአምላካችን ለእግዚአብሔር የሚቀርበው መሥዋዕት የሚቃጠልበትን የማገዶ እንጨት የትኞቹ ጐሣዎች ማቅረብ እንደሚገባቸው እኛ ሕዝቡ፥ ካህናቱና ሌዋውያኑ በየዓመቱ ዕጣ በማውጣት እንወስናለን። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)34 እኛም ካህናቱና ሌዋውያኑ ሕዝቡም፥ እንደ አባቶቻችን ቤቶች በተወሰነ ጊዜ በየዓመቱ ወደ አምላካችን ቤት አምጥተን በሕጉ እንደ ተጻፈ በአምላካችን በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ይቃጠል ዘንድ ስለ ዕንጨት ቍርባን ዕጣ ተጣጣልን፤ See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)34 እኛም፥ ካህናቱና ሌዋውያኑ ሕዝቡም፥ እንደ አባቶቻችን ቤቶች በተወሰነ ጊዜ በየዓመቱ ወደ አምላካችን ቤት አምጥተን በሕጉ እንደ ተጻፈ በአምላካችን በእግዚአብሔር መሠዊያ ላይ ይቃጠል ዘንድ ስለ እንጨት ቁርባን ዕጣ ተጣጣልን፥ See the chapter |