ነህምያ 1:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 እኔ አገልጋይህ ዛሬ በፊትህ ስለ አገልጋዮችህ ስለ እስራኤል ልጆች ሌሊትና ቀን የምጸልየውን ጸሎት ለመስማት ጆሮህ ያድምጥ፥ ዐይኖችህም ይከፈቱ፥ በአንተ ላይ ያደረግነውን የእስራኤልን ልጆች ኃጢአት እናዘዛለሁ፤ እኔና የአባቴ ቤት ኃጢአት አድርገናል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ባሪያህ ስለ አገልጋዮችህ ስለ እስራኤል ሕዝብ ቀንና ሌሊት በፊትህ የሚጸልየውን ጸሎት ለመስማት ጆሮህ ይንቃ፤ ዐይንህም ይከፈት። እኔንና የአባቴን ቤት ጨምሮ እኛ እስራኤላውያን አንተን በመበደል የሠራነውን ኀጢአት እናዘዛለሁ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 እግዚአብሔር ሆይ! አገልጋዮችህ ስለ ሆኑት የእስራኤል ሕዝብ ደኅንነት ቀንና ሌሊት የማቀርበውን ጸሎቴን ስማ፤ እኔንም አስበኝ፤ እኛ እስራኤላውያን የሠራነውንም ኃጢአት እናዘዛለሁ፤ በእርግጥም እኔና የቀድሞ አባቶቼ በደል ሠርተናል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 እኔ ባሪያህ ዛሬ በፊትህ ስለ ባሪያዎችህ ስለ እስራኤል ልጆች ሌሊትና ቀን የምጸልየውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ ጆሮዎችህ ያድምጡ፤ ዐይኖችህም ይከፈቱ፤ በአንተ ላይም ያደረግነውን የእስራኤልን ልጆች ኀጢአት ለአንተ እንናዘዛለን፤ እኔም፥ የአባቴም ቤት በድለናል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 እኔ ባሪያህ ዛሬ በፊትህ ስለ ባሪያዎችህ ስለ እስራኤል ልጆች ሌሊትና ቀን የምጸልየውን ጸሎት ትሰማ ዘንድ ጆሮህ ያድምጥ፤ ዓይኖችህም ይከፈቱ፤ በአንተ ላይም ያደረግነውን የእስራኤልን ልጆች ኃጢአት እናዘዝልሃለሁ፤ እኔና የአባቴም ቤት በድለናል። See the chapter |