Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ናሆም 3:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ለከበባው ውኃ ለራስሽ ቅጂ፥ ምሽግሽን አጠናክሪ፤ ወደ ጭቃው ግቢ፥ ጭቃውንም ርገጪ፥ የጡብ መሥሪያ ያዢ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ለከበባው ውሃ ቅጅ፤ መከላከያሽን አጠናክሪ፤ የሸክላውን ዐፈር ፈልጊ፤ ጭቃውን ርገጪ፤ ጡቡንም ሥሪ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ጠላቶችሽ ከበው በሚያስጨንቁሽ ጊዜ የምትጠጪውን ውሃ ቀድተሽ አዘጋጂ! ምሽጎችሽን አጠናክሪ! ጭቃ ረግጠሽ የሸክላ መሥሪያ አዘጋጂ! ጡብም ሥሪ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ከብበው ያስጨንቁሻልና ውኃን ቅጂ፣ አምባሽን አጠንክሪ፣ ወደ ጭቃ ገብተሽ እርገጪ፣ የጡብን መሠሪያ ያዢ።

See the chapter Copy




ናሆም 3:14
10 Cross References  

እነሆ፥ መልካም ዜና የሚያመጣ፥ ሰላምንም የሚያሰማ ሰው እግር በተራሮች ላይ ነው! ይሁዳ ሆይ በዓሎችሽን አክብሪ፥ ስእለቶችሽን ክፈዪ፤ አጥፊው ፈጽሞ ተቆርጧልና፥ ከእንግዲህም ወዲህ በአንቺ በኩል አያልፍምና።


ፈረሶች ሆይ! ውጡ፤ ሰረገሎችም ሆይ! ንጐዱ፤ ጋሻም የሚያነግቡ የኢትዮጵያና የፉጥ ኃያላን፥ ቀስትንም ይዘው የሚስቡ የሉድ ኃያላን ይውጡ።


ቈፈርኩ ውኃም ጠጣሁ፥ የግብጽንም ወንዞች ሁሉ በእግሬ ጫማ አደረቅኩ።”


እናንተ አሕዛብ፤ ፎክሩ፤ ግን ደንግጡ። በሩቅ አገር ያላችሁ አድምጡ፤ ለጦርነትም ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ደንግጡ፤ ለጦርነትም ተዘጋጁ፤ ነገር ግን ደንግጡ፤


“ጌታ አምላካችን ከአሦር ንጉሥ እጅ ያድነናል” እያለ በራብና በጥም እንድትሞቱ አሳልፎ ለመስጠት የሚያባብላችሁ ሕዝቅያስ አይደለምን?


የሚበትን ከፊት ለፊትሽ መጥቷል፤ ምሽጉን ጠብቂ፥ መንገዱን በደንብ ጠብቂ፤ ወገብሽን አጽኚ፥ ኃይልሽንም እጅግ አበርቺ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements