ናሆም 2:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 ጌታ የያዕቆብን ክብር እንደ እስራኤል ክብር ይመልሳል፤ አጥፊዎች አጥፍተዋቸዋልና፥ የወይናቸውን ቅርንጫፎች አጥፍተዋልና። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 የወታደሮቹ ጋሻ ቀይ ነው፤ ተዋጊዎቹ ቀይ ልብስ ለብሰዋል፤ ዝግጁ በሆኑበት ቀን፣ የሠረገሎቹ ብረት ያብረቀርቃል፤ የጦሩ ዘንግ ይወዛወዛል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 ወታደሮች ቀያይ ጋሻዎችን አንግበዋል፤ ወታደሮቹ ሐምራዊ ልብስ ለብሰዋል፤ እርሱ ሲያሰልፋቸው የሠረገላዎቹ ብረት ያንጸባርቃል፤ ፈረሰኞቹ በፈረስ ላይ ሆነው ይቊነጠነጣሉ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 የኃያላኑ ጋሻ ቀልቶአል፥ ጽኑዓንም ቀይ ልብስ ለብሰዋል። እርሱም በሚያዘጋጅበት ቀን ሰረገሎች እንደ እሳት ይንቦገቦጋሉ፣ የጦሩም ሶመያ ይወዛወዛል። See the chapter |