ናሆም 2:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 አንበሳው ለልጆቹ የሚበቃውን ያህል ነጠቀ፥ ለእንስቶቹም አነቀላቸው፥ ዋሻውን በነጠቀው፥ ጉድጓዱንም በተቦጫጨቀ ሥጋ ሞልቶታል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በእናንተ ላይ ተነሥቼባችኋለሁ፤ ሠረገሎቻችሁን አቃጥዬ አጨሳለሁ፤ ደቦል አንበሶቻችሁን ሰይፍ ይበላል፤ የምትበሉትን በምድር ላይ አልተውላችሁም፤ የመልእክተኞቻችሁም ድምፅ፣ ከእንግዲህ ወዲያ አይሰማም።” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ነነዌ ሆይ! በአንቺ ላይ ተነሥቼአለሁ ይላል የሠራዊት አምላክ፤ ሠረገሎችሽንም አቃጥላለሁ፤ ደቦሎችሽንም ሰይፍ ይበላቸዋል፤ በምድር ላይ በአንቺ ተጠቂ የሚሆን እንዳይኖር አደርጋለሁ፤ የመልእክተኞችሽም ድምፅ ከእንግዲህ ወዲያ አይሰማም። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 እነሆ በአንቺ ላይ ነኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ ሰረገሎችዋንም አቃጥዬ አጤሳለሁ፥ ሰይፍም የአንበሳ ደቦሎችሽን ይበላቸዋል፣ ንጥቂያሽንም ከምድር አጠፋለሁ፥ የመልክተኞችሽን ድምፅ ከእንግዲህ ወዲህ አይሰማም። See the chapter |