ሚክያስ 7:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 እንደ እባብ አፈር ይልሳሉ፥ በምድር እንደሚሳቡ ፍጥረታት እየተንቀጠቀጡ ከምሽጋቸው ይመጣሉ፤ በፍርሃት ወደ ጌታ አምላካችን ይመጣሉ፥ ከአንተ የተነሣ ይፈራሉ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 በደረታቸው እንደሚሳቡ ፍጥረታት፣ እንደ እባብም ትቢያ ይልሳሉ፤ ከዋሻቸው እየተንቀጠቀጡ ይወጣሉ፤ በፍርሀትም ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ይመለሳሉ፤ እናንተንም ይፈራሉ። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17 እንደ እባብና እንደ ሌሎችም ተንፏቃቂ ፍጥረቶች ትቢያ ይልሳሉ፤ ከምሽጎቻቸው ወጥተው እየተንቀጠቀጡ ይመጣሉ፤ በፍርሃትም ወደ አንተ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ይመለሳሉ፤ አንተንም እየፈሩ ይኖራሉ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 እንደ ምድርም ተንቀሳቃሾች እየተንቀጠቀጡ ከግንባቸው ይመጣሉ፥ ፈርተውም ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ይመጣሉ፥ ስለ አንተም ይፈራሉ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 እንደ ምድርም ተንቀሳቃሾች እየተንቀጠቀጡ ከግንባቸው ይመጣሉ፥ ፈርተውም ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ይመጣሉ፥ ስለ አንተም ይፈራሉ። See the chapter |