ሚክያስ 6:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 ትበላለህ፥ ነገር ግን አትጠግብም፥ ባዶነትህም በመካከልህ ይሆናል፤ ትወስዳለህ፥ ነገር ግን ወደ ደህንነት አታመጣም፥ ወደ ደህንነት ያመጣኸውንም ለሰይፍ እሰጣለሁ። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 ትበላለህ፤ ነገር ግን አትጠግብም፤ ሆድህ እንዳለ ባዶውን ይቀራል፤ ታከማቻለህ፤ ነገር ግን አይጠራቀምልህም፤ የሰበሰብኸውን ለሰይፍ አደርገዋለሁና። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 ትበላላችሁ አትጠግቡም፤ ራቡም አይወገድላችሁም፤ ታግበሰብሳላችሁ እንጂ አይከማችላችሁም፤ ያጠራቀማችሁት ሀብት ቢኖርም በጦርነት አጠፋዋለሁ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 ትበላለህ፥ ነገር ግን አትጠግብም፥ ችጋርህም በመካከልህ ይሆናል፥ ትወስዳለህ፥ ነገር ግን አታድንም፥ የምታድነውንም ለሰይፍ እሰጣለሁ። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 ትበላለህ፥ ነገር ግን አትጠግብም፥ ችጋርህም በመካከልህ ይሆናል፥ ትወስዳለህ፥ ነገር ግን አታድንም፥ የምታድነውንም ለሰይፍ እሰጣለሁ። See the chapter |