ሚክያስ 4:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)9 አሁንስ ለምን ጮክ ብልሽ ታለቅሻለሽ? በአንቺ ዘንድ ንጉሥ ስለ ሌለ ነውን? እንደምትወልድ ሴት ምጥ የያዘሽ፥ መካሪሽ ስለ ጠፋ ነውን? See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም9 አሁንስ እንደዚህ የምትጮኺው ለምንድን ነው? ንጉሥ የለሽምን? ምጥ እንደ ያዛት ሴት የተጨነቅሽው፣ መካሪሽ ስለ ጠፋ ነውን? See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም9 እንደዚህ ከፍ አድርገሽ የምትጮኺው፥ ምጥ እንደ ያዛት ሴት የምትጨነቂው ለምንድን ነው? ንጉሥ ስለሌለሽ ነውን? ወይስ አማካሪዎችሽ ሁሉ ስለ ጠፉ ነውን? See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 አሁንስ ለምን ትጮኺአለሽ? እንደምትወልድ ሴት ምጥ የደረሰብሽ፥ ንጉሥ ስለሌለሽ ነውን? ወይስ መካሪ ስለ ጠፋብሽ ነውን? See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)9 አሁንስ ለምን ትጮኺአለሽ? እንደምትወልድ ሴት ምጥ የደረሰብሽ፥ ንጉሥ ስለሌለሽ ነውን? ወይስ መካሪ ስለ ጠፋብሽ ነውን? See the chapter |