Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማቴዎስ 27:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 እርሱም “ምን ክፉ ነገር ሠራና?” አለ፤ እነርሱ ግን “ይሰቀል!” እያሉ አብዝተው ጮኹ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ጲላጦስም፣ “ለምን? ምን ክፉ ነገር አድርጓል?” በማለት ጠየቃቸው። እነርሱ ግን አብዝተው እየጮኹ፣ “ይሰቀል!” አሉ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ገዢውም ለምን? “እርሱ ያደረገው በደል ምንድን ነው?” አላቸው። እነርሱ ግን “ይሰቀል!” እያሉ አብዝተው ጮኹ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 ገዢውም “ምን ነው? ያደረገው ክፋት ምንድር ነው?” አለ፤ እነርሱ ግን “ይሰቀል!” እያሉ ጩኸት አበዙ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 ገዢውም፦ ምን ነው? ያደረገው ክፋት ምንድር ነው? አለ፤ እነርሱ ግን፦ ይሰቀል እያሉ ጩኸት አበዙ።

See the chapter Copy




ማቴዎስ 27:23
16 Cross References  

በታላቅ ድምፅም እየጮኹ ጆሮአቸውን ደፈኑ፤ በአንድ ልብ ሆነውም ወደ እርሱ ሮጡ፤


ብዙ ጥልም በሆነ ጊዜ የሻለቃው ጳውሎስን እንዳይገነጣጥሉት ፈርቶ ጭፍሮቹ ወርደው ከመካከላቸው እንዲነጥቁት ወደ ሰፈሩም እንዲያገቡት አዘዘ።


ጲላጦስም “ታዲያ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን ምን ላድርገው?” አላቸው፤ ሁሉም “ይሰቀል!” አሉ።


ጲላጦስም ይህ ነገር ሁከት ከማስነሳት በስተቀር ምንም እንደማይጠቅም ባየ ጊዜ፥ ውሃ ወስዶ “እኔ ከዚህ ሰው ደም ንጹሕ ነኝ፤ ጉዳዩ የእናንተ ነው፤” ብሎ በሕዝቡ ፊት እጁን ታጠበ።


ጲላጦስም ለካህናት አለቆችና ለሕዝቡ “በዚህ ሰው ላይ ምንም በደል አላገኘሁበትም፤” አለ።


ለሞትም የሚያደርስ ምክንያት አንድ ስንኳ ባያገኙበት፥ ይገድለው ዘንድ ጲላጦስን ለመኑት፤


ዓይኑን የሚዘጋ ጠማማ አሳብን ያስባል፥ ከንፈሩን የሚነክስ ክፋትን ይፈጽማል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements