Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማቴዎስ 23:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ደግሞም ‘ማንም በመሠዊያው ቢምል ምንም አይደለም፤ ማንም በላዩ ላይ ባለው መባ ቢምል ግን በመሐላው ይያዛል፤’ ትላላችሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እንዲሁም፣ ‘ማንም በመሠዊያው ቢምል ምንም አይደለም፤ ነገር ግን በላዩ ላይ ባለው መባ ቢምል መሐላው ይደርስበታል’ ትላላችሁ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እንዲሁም ‘ሰው በመሠዊያው ቢምል ምንም አይደለም’፤ ‘በመሠዊያው ላይ ባለው መባ ቢምል ግን በመሐላው ይያዛል’ ትላላችሁ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ደግማችሁም ‘ማንም በመሠዊያው የሚምል ምንም የለበትም፤ ማንም በላዩ ባለው መባ የሚምል ግን በመሐላው ይያዛል፤’ ትላላችሁ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ደግማችሁም፦ ማንም በመሠዊያው የሚምል ምንም የለበትም፤ ማንም በላዩ ባለው መባ የሚምል ግን በመሐላው ይያዛል ትላላችሁ።

See the chapter Copy




ማቴዎስ 23:18
7 Cross References  

“እናንተ ዕውራን መሪዎች ‘ማንም በቤተ መቅደስ ቢምል ምንም አይደለም፥ ማንም በቤተ መቅደስ ወርቅ ቢምል ግን በመሐላው ይያዛል፤’ የምትሉ ወዮላችሁ።


እናንተ ዕውሮችና ሞኞች! የትኛው ይበልጣል? ወርቁ ወይስ ወርቁን የቀደሰው ቤተ መቅደስ?


እናንተ ዕውሮች! የትኛው ይበልጣል? መባው ወይስ መባውን የሚቀድሰው መሠዊያው?


ሰው ለጌታ ስእለት ቢሳል፥ ወይም ራሱን በመሐላ ቢያስር፥ ቃሉን አያፍርስ፤ ከአፉ እንደ ወጣው ሁሉ ያድርግ።


“ሰው በባልንጀራው ላይ ኃጢአት ቢሠራ፥ እርሱም መሐላ እንዲምል ቢደረግ፥ እርሱም መጥቶ በዚህ ቤት በመሠዊያህ ፊት ቢምል፥


እናንተ ግን አንድ ሰው አባቱን ወይም እናቱን፥ ከእኔ ማግኘት የሚገባችሁን ርዳታ ሁሉ ቁርባን ይኸውም መባ አድርጌለሁ ቢላቸው፥


የተገረዘ ሰው ሁሉ ሕግን በሙሉ የመፈጸም ግዴታ አለበት ብዬ ደግሜ እመሰክራለሁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements