ማቴዎስ 2:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፤ ወድቀውም ሰገዱለት፤ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅ፥ ዕጣንና ከርቤ አቀረቡለት። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ወደ ቤትም በገቡ ጊዜ ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋራ አዩ፤ ተንበርክከውም ሰገዱለት። ሣጥኖቻቸውን ከፍተው ወርቅ፣ ዕጣን፣ ከርቤም አቀረቡለት። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር ሆኖ አዩት፤ ተደፍተውም ሰገዱለት፤ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው የወርቅ፥ የዕጣንና የከርቤ ስጦታ አቀረቡለት። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፤ ወድቀውም ሰገዱለት፤ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋር አዩት፥ ወድቀውም ሰገዱለት፥ ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና ዕጣን ከርቤም አቀረቡለት። See the chapter |