Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማቴዎስ 1:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 እጮኛዋ ዮሴፍ ጻድቅ ስለ ነበረ ሊያጋልጣት አልፈለገም፥ በስውርም ሊተዋት አሰበ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ዕጮኛዋ ዮሴፍ ጻድቅ ሰው ስለ ነበርና ማርያምን በሰው ፊት ሊያጋልጣት ስላልፈለገ በስውር ሊተዋት ወሰነ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 እጮኛዋ ዮሴፍ ደግ ሰው ስለ ነበረ፥ ማርያምን በሰው ፊት ሊያጋልጣት አልፈለገም፤ ስለዚህ በስውር ሊተዋት አሰበ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 እጮኛዋ ዮሴፍም ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት አሰበ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 እጮኛዋ ዮሴፍም ጻድቅ ሆኖ ሊገልጣት ስላልወደደ በስውር ሊተዋት አሰበ።

See the chapter Copy




ማቴዎስ 1:19
15 Cross References  

እነሆም፥ በኢየሩሳሌም ስምዖን የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ ይህም ሰው የእስራኤልን መጽናናት የሚጠብቅ፥ ጻድቅና ትጉህም ነበረ፤ መንፈስ ቅዱስም በእርሱ ላይ ነበረ።


ምክንያቱም ዮሐንስ ጻድቅና ቅዱስ ሰው መሆኑን ሄሮድስ በማወቁ ይፈራውና ይጠብቀው ነበር። ዮሐንስ የሚናገረውን ሲሰማ ሄሮድስ ቢታወክም በደስታ ያዳምጠው ነበር።


“ማናቸውም ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ወይም ከባልጀራው ሚስት ጋር ቢያመነዝር አመንዝራውና አመንዝራይቱ ፈጽመው ይገደሉ።


ከሦስት ወር በኋላ፥ “ምራትህ ትዕማር ዘማዊ ሆናለች፤ ከዚህም የተነሣ አርግዛለች” ተብሎ ለይሁዳ ተነገረው። ይሁዳም፥ “አውጧትና በእሳት ተቃጥላ ትሙት” አለ።


እነርሱም፥ “ሙሴማ የፍች ወረቀት ጽፎ እንዲፈታት ፈቅዷአል” አሉ።


“ማናቸውም ሰው በባርነት ሥር ካለች ሴት ጋር ቢተኛ፥ እርሷም ለሌላ ሰው ታጭታ ነገር ግን ሙሉ ለሙሉ ያልተዋጀች ወይም አርነት ያልወጣች ብትሆን፥ ይህ አድራጎት ቅጣት ይረኖረዋል፤ ሆኖም አርነት አልወጣችምና አይገደሉም።


የኖኅ ትውልድ እንደሚከተለው ነው። ኖኅም ጻድቅ፥ በትውልዱም በደል ያልተገኘበት ሰው ነበረ፥ ኖኅም እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው።


እነርሱም፦ “ጻድቅ ሰው እግዚአብሔርንም የሚፈራ በአይሁድም ሕዝብ ሁሉ የተመሰከረለት የመቶ አለቃ ቆርኔሌዎስ ወደ ቤቱ ያስመጣህ ዘንድ ከአንተም ቃልን ይሰማ ዘንድ ከቅዱስ መልአክ ተረዳ፤” አሉት።


“ነገሩ ግን እውነት ቢሆን፥ በብላቴናይቱም ድንግልናዋ ባይገኝ፥


በነጋም ጊዜ ምድሩን አላወቁትም፤ ነገር ግን የአሸዋ ዳር ያለውን የባሕር ሰርጥ ተመለከቱ፤ ቢቻላቸውም መርከቡን ወደዚያ ይገፉ ዘንድ ቆረጡ።


በዚህም እርግጠኛ ስለነበርኩ፥ በእጥፍ እንድትጠቀሙ አስቀድሜ ወደ እናንተ መምጣት ፈልጌ ነበር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements