Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማርቆስ 7:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ደግሞም፥ እንዲህ አላቸው፤ “የራሳችሁን ወግ ለመጠበቅ ስትሉ፥ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የምትተውበት ዘዴ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ደግሞም፣ እንዲህ አላቸው፤ “የራሳችሁን ወግ ለመጠበቅ ስትሉ፣ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ የምትተዉበት ዘዴ አላችሁ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፤ “ወጋችሁን ለመጠበቅ ስትሉ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ትተዋላችሁ፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እንዲህም አላቸው “ወጋችሁን ትጠብቁ ዘንድ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እጅግ ንቃችኋል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 እንዲህም አላቸው፦ ወጋችሁን ትጠብቁ ዘንድ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ እጅግ ንቃችኋል።

See the chapter Copy




ማርቆስ 7:9
16 Cross References  

የእግዚአብሔርን ጸጋ አልናቅሁም፤ ጽድቅ በሕግ በኩል የሚገኝ ከሆነ እንግዲያውስ ክርስቶስ የሞተው በከንቱ ነው ማለት ነዋ!


ምድርም በነዋሪዎቿ ረክሳለች፥ ሕጉን ተላልፈዋልና፥ ሥርዓቱንም ለውጠዋልና፥ የዘለዓለሙንም ቃል ኪዳን አፍርሰዋል።


ጌታም፦ ይህ ሕዝብ በአፉ ወደ እኔ ይቀርባል፥ በከንፈሮቹም ያከብረኛል፥ ልቡ ግን ከእኔ የራቀ ነው፤ በሰዎች ሥርዓትና ትምህርት ብቻ ይፈራኛል።


ስለዚህ ለትውልድ በምታስተላልፉት ወግ የእግዚአብሔርን ቃል ትሽራላችሁ፤ ይህን የመሰለም ብዙ ነገር ታደርጋላችሁ።”


ፈሪሳውያንና አይሁድ ሁሉ የአባቶችን ወግ ለመጠበቅ ሲሉ፥ በሥርዓቱ መሠረት እጃቸውን በጥንቃቄ ሳይታጠቡ አይበሉም ነበርና።


ለጌታ የሥራ ጊዜ ነው፥ ሕግህንም ሻሩት።


እርሱም ሰው የሚያመልከውን ነገር ወይም አማልክት ነን ከሚሉት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ በማድረግና በመቃወም፦ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ” ብሎ ያውጃል፤ በእግዚአብሔርም ቤተ መቅደስ ይቀመጣል።


ስለዚህ ሕግን በእምነት እንሽራለንን? በጭራሽ! ነገር ግን ሕግን እናጸናለን።


ፈሪሳውያንና ጸሐፍትም፥ “ደቀ መዛሙርትህ እንደ አባቶች ወግ በመኖር ፈንታ ባልታጠበ እጃቸው ለምን እንጀራ ይበላሉ?” ብለው ጠየቁት።


ምክንያቱም አንዱ መጥቶ እኛ ያልሰበክነውን ሌላ ኢየሱስ ቢሰብክ፥ ወይም ያላገኛችሁትን ልዩ መንፈስ ወይም ያልተቀበላችሁትን ልዩ ወንጌል ሆኖ ብታገኙት፥ በመልካምነታችሁ ትታገሡታላችሁ።


ለአባቶች ወግ ከመጠን በላይ ቅናት ስለ ነበረኝ፥ በአይሁዳዊነት ወገኖቼ ከነበሩት እኩዮቼ ብዙዎችን እበልጥ ነበር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements