ማርቆስ 2:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 በአረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ የወይን ጠጁ አቁማዳውን ያፈነዳል፤ የወይኑም ጠጅ ይፈሳል፤ አቁማዳውም ይጠፋል፤ አዲሱን የወይን ጠጅ ግን በአዲስ አቁማዳ ያኖራሉ።” See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 እንዲሁም አዲስ የወይን ጠጅ በአሮጌ አቍማዳ የሚያስቀምጥ የለም፤ ይህ ከተደረገማ የወይን ጠጁ አቍማዳውን ያፈነዳዋል፤ የወይን ጠጁም አቍማዳውም ይበላሻሉ። ስለዚህ አዲስ የወይን ጠጅ መቀመጥ ያለበት በአዲስ አቍማዳ ነው።” See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 እንዲሁም በአረጀ የወይን ጠጅ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን የወይን ጠጁ አቁማዳውን ያፈነዳዋል፤ የወይን ጠጁም ይፈስሳል፤ አቁማዳውም ከንቱ ይሆናል። ስለዚህ ለአዲስ የወይን ጠጅ አዲስ አቁማዳ ያስፈልገዋል፤” አላቸው። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 በአረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ የወይን ጠጁ አቁማዳውን ያፈነዳል፤ የወይኑም ጠጅ ይፈሳል፤ አቁማዳውም ይጠፋል፤ አዲሱን የወይን ጠጅ ግን በአዲስ አቁማዳ ያኖራሉ።” See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 በአረጀ አቁማዳም አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ የወይን ጠጁ አቁማዳውን ያፈነዳል የወይኑም ጠጅ ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል አዲሱን የወይን ጠጅ ግን በአዲስ አቁማዳ ያኖራሉ። See the chapter |