Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ማርቆስ 1:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ስለዚህ መጥምቁ ዮሐንስ በበረሓ እያጠመቀና ለኃጢአት ስርየት የንስሓ ጥምቀት እየሰበከ መጣ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ስለዚህ መጥምቁ ዮሐንስ በበረሓ እያጠመቀና ለኀጢአት ስርየት የንስሓ ጥምቀት እየሰበከ መጣ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ስለዚህ መጥምቁ ዮሐንስ “የኃጢአትን ይቅርታ እንድታገኙ፥ ንስሓ ገብታችሁ ተጠመቁ” በማለት በበረሓ እያወጀ መጣ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ዮሐንስ በምድረ በዳ እያጠመቀ የንስሐንም ጥምቀት ለኀጢአት ስርየት እየሰበከ መጣ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ዮሐንስ በምድረ በዳ እያጠመቀ የንስሐንም ጥምቀት ለኃጢአት ስርየት እየሰበከ መጣ።

See the chapter Copy




ማርቆስ 1:4
11 Cross References  

ዮሐንስም ደግሞ በሳሌም አቅራቢያ በሄኖን፥ በዚያ ብዙ ውሃ ነበርና፥ ያጠምቅ ነበር፤ እየመጡም ይጠመቁ ነበር፤


ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ በእርሱ ይጠመቁ ነበር።


እንዲሁም በኀጢአታቸው ስርየት የመዳንን እውቀት ለሕዝቡ ትሰጣለህ፤


አሁንስ ለምን ትዘገያለህ? ተነሣና ስሙን እየጠራህ ተጠመቅ፤ ከኃጢአትህም ታጠብ።’


ዮሐንስ ከሰበከው ጥምቀት በኋላ ከገሊላ ጀምሮ በይሁዳ ሁሉ የሆነውን ነገር እናንተ ታውቃላችሁ።


“እኔ ለንስሐ በውሃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን ለመሸከም የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃችኋል፤


የይሁዳ አገር በሞላ፥ የኢየሩሳሌም ሰዎች በጠቅላላ ወደ እርሱ በመሄድ ኀጢአታቸውን እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ እጅ ተጠመቁ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements