ሚልክያስ 2:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)14 እናንተም፦ ለምን ይህ ሆነ? ትላላችሁ። ምክንያቱም ሚስትህን አታልለሃታልና ጌታ በአንተና በልጅነት ሚስትህ መካከል ምስክር ስለ ሆነ ነው፤ እርሷም ጓደኛህና የቃል ኪዳን ሚስትህ ነበረች። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም14 እናንተም፣ “ለምን ይህ ሆነ?” ብላችሁ ትጠይቃላችሁ። ይህ የሆነው የትዳር ጓደኛህን፣ አጋርህንና የቃል ኪዳን ሚስትህን አታልለሃታልና፣ እግዚአብሔር በአንተና በወጣትነት ሚስትህ መካከል ላለው ቃል ኪዳን ምስክር ስለ ሆነ ነው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም14 “ስለምን መሥዋዕታችንን አይቀበልም?” ብላችሁ ትጠይቃላችሁ፤ እግዚአብሔር መሥዋዕታችሁን የማይቀበለው የቃል ኪዳን ጓደኞቻችሁ ለሆኑት ለወጣትነት ሚስቶቻችሁ ታማኝነታችሁን ስላፈረሳችሁ ነው፤ በእናንተም መካከል እግዚአብሔር ምስክር ነበር። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)14 እናንተም፦ ስለ ምንድር ነው? ብላችኋል። ሚስትህ ባልንጀራህና የቃል ኪዳንህ ሚስት ሆና ሳለች እርስዋን አታልለሃታልና እግዚአብሔር በአንተና በልጅነት ሚስትህ መካከል ምስክር ስለ ሆነ ነው። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)14 እናንተም፦ ስለ ምንድር ነው? ብላችኋል። ሚስትህ ባልንጀራህና የቃል ኪዳንህ ሚስት ሆና ሳለች እርስዋን አታልለሃታልና እግዚአብሔር በአንተና በልጅነት ሚስትህ መካከል ምስክር ስለ ሆነ ነው። See the chapter |