Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 9:59 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

59 ሌላውንም፦ “ተከተለኝ፤” አለው። እርሱ ግን፦ “ጌታ ሆይ! መጀመሪያ ሄጄ አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ፤” አለ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

59 ሌላውን ሰው ግን፣ “ተከተለኝ” አለው። ሰውየውም፣ “ጌታ ሆይ፤ አስቀድሜ ሄጄ አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ” አለው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

59 ሌላውንም ሰው “ተከተለኝ!” አለው። ሰውየው ግን “ጌታ ሆይ! መጀመሪያ ሄጄ አባቴን እንድቀብር ፍቀድልኝ፤” አለው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

59 ሌላ​ው​ንም፥ “ተከ​ተ​ለኝ” አለው፤ እርሱ ግን፥ “አቤቱ፥ በፊት ሄጄ አባ​ቴን እን​ድ​ቀ​ብ​ረው ፍቀ​ድ​ልኝ” አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

59 ሌላውንም፦ ተከተለኝ አለው። እርሱ ግን፦ ጌታ ሆይ አስቀድሜ ልሂድና አባቴን እቀብር ዘንድ ፍቀድልኝ አለ።

See the chapter Copy




ሉቃስ 9:59
8 Cross References  

በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አላቸው “ሊከተለኝ የሚወድ ራሱን ይካድ፥ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።


ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ፈልጉ፥ እነዚህም ሁሉ ይጨመሩላችኋል።


በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ በሬዎቹን ትቶ ወደ ኤልያስ በመሮጥ “አባትና እናቴን ስሜ እንድሰናበት ፍቀድልኝ ከዚያም በኋላ እከተልሃለሁ” አለው። ኤልያስም “እሺ፥ ተመልሰህ ሂድ፤ እኔ አልከለክልህም!” ሲል መለሰለት።


የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ይህ ሕዝብ፦ ዘመኑ አልደረሰም፥ የጌታ ቤት የሚሠራበት ዘመን አልደረሰም ይላል።”


ኢየሱስም ከዚያ አልፎ ሲሄድ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው በቀረጥ መቀበያ ስፍራ ተቀምጦ አየውና “ተከተለኝ” አለው። ተነሥቶም ተከተለው።


ኢየሱስም፦ “ሙታኖቻቸውን እንዲቀብሩ ሙታንን ተዋቸው፤ አንተስ ሄደህ የእግዚአብሔርን መንግሥት አስተምር፤” አለው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements