Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 8:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ከዕለታቱም በአንዱ ቀንም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ታንኳ ገብቶ፦ “ወደ ባሕር ማዶ እንሻገር፤” አላቸው፤ እነርሱም ለመሄድ ተነሡ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ከዕለታቱ በአንድ ቀን፣ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ጀልባ ላይ ወጣ፤ ኢየሱስም፤ “ወደ ባሕሩ ማዶ እንሻገር” አላቸው፤ ከዚያም ጕዞ ቀጠሉ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 አንድ ቀን ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በጀልባ ተሳፈረና “ወደ ባሕሩ ማዶ እንሻገር፤” አላቸው፤ እነርሱም ለመሄድ ተነሡ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ከዕ​ለ​ታት በአ​ን​ዲት ቀንም እን​ዲህ ሆነ፤ እርሱ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር ወደ ታንኳ ወጣና፥ “ኑ ወደ ባሕሩ ማዶ እን​ሻ​ገር” አላ​ቸው እነ​ር​ሱም ሄዱ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ከዕለታቱም በአንዱ እርሱ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ታንኳ ገብቶ፦ ወደ ባሕር ማዶ እንሻገር አላቸው፤ ተነሡም።

See the chapter Copy




ሉቃስ 8:22
12 Cross References  

ወዲያውም እርሱ ሕዝቡን እያሰናበተ ሳለ፥ ደቀመዛሙርቱ በጀልባ ወደ ቤተሳይዳ ቀድመውት እንዲሻገሩ አዘዛቸው፤


እየሄዱም ሳሉ ኢየሱስ እንቅልፍ ወሰደው። ዓውሎ ነፋስም በሐይቁ ላይ ተነሣ፤ ውኃውም ታንኳይቱን ይሞላ ነበር፤ እነርሱም በአደጋ ላይ ስለ ነበሩ ተጨንቀው ነበር።


እርሱም በጌንሳሬጥ ባሕር ዳር ቆሞ ሳለ፥ ብዙ ሰዎች የእግዚአብሔርን ቃል ለመስማት በዙርያው ይጋፉ ነበር፤


ከዚያም ትቷቸው በጀልባ ወደ ማዶ ተሻገረ።


ወዲያውም ሕዝቡን እስኪያሰናብት ድረስ ደቀመዛሙርቱ ወደ ጀልባ ገብተው ወደ ማዶ እንዲቀድሙት ግድ አላቸው።


ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ወደ ገሊላ ባሕር ማዶ ተሻገረ፤ እርሱም የጥብርያዶስ ባሕር ነው።


ኢየሱስ እንደገና በጀልባ ወደ ማዶ በተሻገረ ጊዜ፥ ብዙ ሕዝብ በዙሪያው ተሰባሰበ፤ በባሕሩም አጠገብ እንዳለ፤


ኢየሱስ ብዙ ሰዎች በአጠገቡ ሲሰበሰቡ ወደ ማዶ እንዲሻገሩ አዘዘ።


አጋንንቱም ከሰውዬው ወጥተው ወደ ዐሣማዎቹ ገቡ፤ መንጋውም ከአፋፉ ወደ ሐይቁ ተጣድፎ በመውረድ ሰጠመ።


በእስያም ዳርቻ ወዳሉ ስፍራዎች ይሄድ ዘንድ ባለው በአድራሚጢስ መርከብ ገብተን ተነሣን፤ የመቄዶንያም ሰው የሆነ የተሰሎንቄው አርስጥሮኮስ ከእኛ ጋር ነበረ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements