Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 8:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ከዚህም በኋላ ኢየሱስ እየሰበከና ስለ እግዚአብሔር መንግሥት የምሥራች እያበሠረ በየከተማውና በየመንደሩ ያልፍ ነበር፤ ዐሥራ ሁለቱም ከእርሱ ጋር ነበሩ፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት የምሥራች ቃል እየሰበከ በየከተማውና በየመንደሩ ዐለፈ። ዐሥራ ሁለቱም ከርሱ ጋራ ነበሩ፤

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ከዚህም በኋላ ኢየሱስ በየከተማውና በየመንደሩ የእግዚአብሔርን መንግሥት እየሰበከና የምሥራች እያበሠረ ያልፍ ነበር፤ ዐሥራ ሁለቱም አብረውት ነበሩ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ከዚ​ህም በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ በየ​ከ​ተ​ማ​ዉና በየ​መ​ን​ደሩ ተመ​ላ​ለሰ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም መን​ግ​ሥት ሰበ​ከ​ላ​ቸው፤ አስ​ተ​ማ​ራ​ቸ​ውም፤ ዐሥራ ሁለቱ ደቀ መዛ​ሙ​ር​ትም ከእ​ርሱ ጋር ነበሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ከዚህም በኋላ እየሰበከና ስለ እግዚአብሔር መንግሥት የምሥራች እየተናገረ በየከተማይቱ በየመንደሩም ያልፍ ነበር፤

See the chapter Copy




ሉቃስ 8:1
18 Cross References  

ኢየሱስም በምኵራቦቻቸው እያስተማረ፥ የመንግሥትን ወንጌል እየሰበከ፥ በሕዝቡ መካከል ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዘዋወር ነበር።


ካልተላኩስ እንዴት ይሰብካሉ? “መልካሙን ዜና የሚያበሥሩ እግሮቻቸው እንዴት ውብ ናቸው!” ተብሎ እንደተጻፈው ነው።


እኛም ለአባቶች የተሰጠውን ተስፋ የምስራቹን ለእናንተ እንሰብካለን፤


እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፤ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፤ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤


“የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድሆች መልካም ዜናን እንዳበሥር ቀብቶኛልና፤ ለታሰሩትም መፈታትን ለዐይነ ስውሮችም ማየትን እንዳውጅ፥ የተጨቆኑትንም ነጻ እንዳወጣ


ስለዚህ ወደ ምኵራባቸው እየገባ በመስበክና አጋንንትን በማስወጣት በመላዋ ገሊላ ይዘዋወር ጀመር።


የመንግሥቱን ቃል ሰምቶ የማያስተውል ሁሉ፥ ክፉው መጥቶ በልቡ የተዘራውን ይነጥቀዋል፤ በመንገድ ዳር የተዘራው ይህ ነው።


ኢየሱስ ዐሥራ ሁለቱን ደቀ መዛሙርቱን ማዘዝ በፈጸመ በኋላ፥ በከተሞቻቸው ሊያስተምርና ሊሰብክ ሄደ።


ኢየሱስም በምኵራቦቻቸው እያስተማረ፥ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ፥ በሽታንና ሕማምን ሁሉ እየፈወሰ፥ በከተሞችና በመንደሮች ሁሉ ይዞር ነበር።


ሕፃኑም አደገ፤ በመንፈስም ጠነከረ፤ ለእስራኤልም እስከ ታየበት ቀን ድረስ በምድረ በዳ ኖረ።


ወጥተውም ወንጌልን እየሰበኩና በሁሉ ስፍራ እየፈወሱ በየመንደሩ ያልፉ ነበር።


አንድ ቀንም ሕዝቡን በቤተ መቅደስ ሲያስተምር ወንጌልንም ሲሰብክላቸው፥ የካህናት አለቆችና ጻፎች ከሽማግሌዎች ጋር ወደ እርሱ ቀረቡና


Follow us:

Advertisements


Advertisements