Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 6:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 እነሆ በሌላ ሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገብቶ አስተማረ፤ በዚያም ቀኝ እጁ የሰለለ ሰው ነበረ፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 በሌላ ሰንበት ቀንም ወደ ምኵራብ ገብቶ ያስተምር ነበር፤ በዚያም ቀኝ እጁ የሰለለ አንድ ሰው ነበረ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 በሌላም ሰንበት ቀን ኢየሱስ ወደ ምኲራብ ገብቶ ያስተምር ነበር፤ እዚያም ቀኝ እጁ ሽባ የሆነ አንድ ሰው ነበር።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ከዚ​ህም በኋላ በሌ​ላ​ይቱ ሰን​በት ወደ ምኵ​ራቡ ገባና አስ​ተ​ማ​ራ​ቸው፤ በዚ​ያም ቀኝ እጁ የሰ​ለ​ለች ሰው ነበረ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 በሌላው ሰንበትም ወደ ምኵራብ ገብቶ አስተማረ፤ በዚያም ቀኝ እጁ የሰለለች ሰው ነበረ፤

See the chapter Copy




ሉቃስ 6:6
14 Cross References  

በእነዚህም ውስጥ ብዙ ድኩማን፥ ዐይነ ሥውሮች፥ አንካሶችም ሰውነታቸውም የሰለለ ብዙ ሰዎች ይተኙ ነበር።


የገሊላ ከተማም ወደ ሆነችው ወደ ቅፍርናሆም ወረደ። በሰንበትም ያስተምራቸው ነበር፤


ወዳደገበትም ወደ ናዝሬት መጣ፤ እንደተለመደው በሰንበት ቀን ወደ ምኵራብ ገባ፤ ሊያነብም ተነሣ።


ኢየሱስም በምኵራቦቻቸው እያስተማረ፥ የመንግሥትን ወንጌል እየሰበከ፥ በሕዝቡ መካከል ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዘዋወር ነበር።


ከፈሪሳውያንም አንዳንዶቹ “ይህ ሰው ሰንበትን አያከብርምና ከእግዚአብሔር አይደለም፤” አሉ። ሌሎች ግን “ኃጢአትኛ ሰው እንደነዚህ ያሉ ምልክቶችን ሊያደርግ እንዴት ይችላል?” አሉ። በመካከላቸውም መለያየት ሆነ።


ኢየሱስም መልሶ “በሰንበት መፈወስ ተፈቅዶአልን ወይስ አልተፈቀደም?” ብሎ ሕግ አዋቂዎችንና ፈሪሳውያንን ጠየቀ።


በሰንበት ቀንም ከምኵራቦቹ በአንዱ ያስተምር ነበር።


እነሆ፥ በሰንበት ቀን በእርሻ መካከል ሲያልፍ ሳለ ደቀመዛሙርቱ እሸት ቀጥፈው በእጃቸው እያሹ ይበሉ ነበር።


ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ እጁን አንሥቶ ወደ ነቢዩ በማመልከት! “ያዙት!” የሚል ትእዛዝ ሰጠ፤ የንጉሡም ክንድ ወዲያውኑ ድርቅ ብሎ ሽባ ስለ ሆነ የዘረጋውን እጁን መመለስ አልቻለም።


መንጋውን ለሚተው ለማይረባ እረኛ ወዮለት! ሰይፍ ክንዱንና ቀኝ ዓይኑን ይውጋው፤ ክንዱም ፈጽማ ትሰልስል፤ ቀኝ ዓይኑም ፈጽማ ትታወር።


እርሱም “የሰው ልጅ የሰንበት ጌታ ነው፤” አላቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements