ሉቃስ 6:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)23 እነሆ፥ ዋጋችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና፤ በዚያን ቀን ተደሰቱ፤ በደስታም ዝለሉ፤ አባቶቻቸው ነቢያትን እንዲህ ያደርጉባቸው ነበርና። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም23 “እነሆ፤ ወሮታችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና፣ በዚያ ቀን ደስ ይበላችሁ፤ ፈንድቁም፤ የቀድሞ አባቶቻቸውም በነቢያት ላይ ያደረጉት ይህንኑ ነበርና። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም23 በሰማይ ዋጋችሁ ትልቅ ነውና ይህ ሁሉ ሲደርስባችሁ የተባረካችሁ ናችሁ! ሐሴትም አድርጉ፤ የቀድሞ አባቶቻቸውም በነቢያት ላይ እንዲህ ያለውን ክፋት አድርገውባቸው ነበር። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 ያንጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ በደስታም ዝለሉ፤ ዋጋችሁ በሰማይ ብዙ ነውና፤ አባቶቻቸውም ነቢያትን እንዲሁ አድርገዋቸው ነበርና። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)23 እነሆ፥ ዋጋችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና በዚያን ቀን ደስ ይበላችሁ ዝለሉም፤ አባቶቻቸው ነቢያትን እንዲህ ያደርጉባቸው ነበርና። See the chapter |