Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 5:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 እነርሱም እንዲህ አሉት፦ “የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት አዘውትረው ይጾማሉ፤ ጸሎትም ያደርሳሉ፤ የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርትም እንዲሁ ያደርጋሉ፤ የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን ይበላሉ ይጠጣሉም።”

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 እነርሱም፣ “የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት አብዛኛውን ጊዜ ይጾማሉ፤ ይጸልያሉ፤ የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርትም እንደዚሁ ያደርጋሉ፤ የአንተዎቹ ግን ይበላሉ፤ ይጠጣሉ” አሉት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 አንዳንድ ሰዎች ኢየሱስን፦ “የዮሐንስና የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርት ብዙ ጊዜ ይጾማሉ፤ ይጸልያሉም፤ የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን ሁልጊዜ የሚበሉትና የሚጠጡት ለምንድን ነው?” በማለት ጠየቁት።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 እነ​ር​ሱም፥ “የዮ​ሐ​ንስ ደቀ መዛ​ሙ​ርት ስለ​ምን በብዙ ይጾ​ማሉ? ጸሎ​ትስ ስለ​ምን ያደ​ር​ጋሉ? የፈ​ሪ​ሳ​ው​ያን ወገ​ኖች የሆ​ኑ​ትም ስለ​ምን እን​ዲሁ ያደ​ር​ጋሉ? ያንተ ደቀ መዛ​ሙ​ርት ግን ለምን ይበ​ላሉ? ይጠ​ጣ​ሉም?” አሉት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 እነርሱም፦ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት ስለ ምን ብዙ ይጦማሉ ጸሎትስ ስለ ምን ያደርጋሉ፥ ደግሞም የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርት ስለ ምን እንደዚሁ ያደርጋሉ፤ የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን ይበላሉ ይጠጣሉም? አሉት።

See the chapter Copy




ሉቃስ 5:33
20 Cross References  

የመበለቶችን ቤት የሚበሉ፥ ጸሎታቸውንም በማስረዘም የሚያመካኙ ናቸው፤ እነዚህ የባሰ ፍርድ ይቀበላሉ፤” አለ።


በየሳምንቱ ሁለት ጊዜ እጾማለሁ፤ ከማገኘውም ሁሉ አሥራት እሰጣለሁ፤’ አለ።


ጌታም “ተነሥተህ ቅን ወደ ሚባለው መንገድ ሂድ፤ በይሁዳ ቤትም ሳውል የሚሉትን አንድ የጠርሴስ ሰው ፈልግ፤


በዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና በአይሁድ መካከልም ስለ ማንጻት ሥርዓት ክርክር ተነሣ።


በማግሥቱ ዮሐንስ ከሁለት ደቀመዛሙርቱ ጋር እንደገና እዚያ ቆሞ ነበር፤


እርሱም በአንድ ስፍራ ይጸልይ ነበር፤ በጨረሰም ጊዜ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ፦ “ጌታ ሆይ! ዮሐንስ ደቀ መዛሙርቱን እንዳስተማረ እንዲሁ መጸለይን አስተምረን፤” አለው።


በረጅም ጸሎታቸው እያሳበቡ የመበለቶችን ቤት ያራቁታሉ፤ እነዚህ የባሰ ፍርድ ይቀበላሉ።”


“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰዎች ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ ራሳችሁ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።


ስትበሉና ስትጠጡስ፥ የምትበሉትና የምትጠጡት ለራሳችሁ አይደለምን?


እጆቻቸሁን ለጸሎት ወደ እኔ ስትዘረጉ፤ ዐይኖቼን ከእናንተ እሰውራለሁ፤ አብዝታችሁ ብትጸልዩም እንኳ አልሰማችሁም፤ እጆቻችሁ በደም ተበክለዋል፤


ሕግን ከመስማት ጆሮውን የሚመልስ ጸሎቱ እንኳን ሳይቀር አስጸያፊ ናት።


እርሷም እስከ ሰማኒያ አራት ዓመቷ ድረስ መበለት ነበረች፤ በጾምና በጸሎትም ሌሊትና ቀን እያገለገለች ከመቅደስ አትለይም ነበር።


ኀጢአተኞችን ወደ ንስሓ ልጠራ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁም።”


ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፦ “ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሚዜዎችን ልታጾሙ አትችሉም፤ ትችላላችሁን?


Follow us:

Advertisements


Advertisements