Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 5:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ሌዊም ታላቅ ግብዣ በቤቱ አደረገለት፤ ከቀራጮችና ከሌሎችም ብዙ ሕዝብ በማዕድ ከእነርሱ ጋር ተቀምጠው ነበር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ሌዊም ለኢየሱስ በቤቱ ትልቅ ግብዣ አደረገ፤ ብዙ ቀረጥ ሰብሳቢዎችና ሌሎች ሰዎችም ከእነርሱ ጋራ በማእድ ተቀምጠው ነበር።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ከዚህም በኋላ ሌዊ በቤቱ ለኢየሱስ ክብር ትልቅ ግብዣ አደረገ፤ በግብዣውም ላይ ብዙ ቀራጮችና ሌሎችም ብዙ ሰዎች ተገኝተው ነበር።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ሌዊም በቤቱ ታላቅ ግብዣ አደ​ረ​ገ​ለት፤ ብዙ ሰዎ​ችም ከእ​ርሱ ጋር ነበሩ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ለምሳ ተቀ​ም​ጠው የነ​በሩ ቀራ​ጮ​ችና ኀጢ​አ​ተ​ኞች፥ ሌሎ​ችም ብዙ​ዎች ነበሩ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ሌዊም በቤቱ ታላቅ ግብዣ አደረገለት፤ ከእነርሱም ጋር በማዕድ ተቀምጠው የነበሩ ከቀራጮችና ከሌሎች ሰዎች ብዙ ሕዝብ ነበሩ።

See the chapter Copy




ሉቃስ 5:29
9 Cross References  

ቀራጮችና ኀጢአተኞችም ሁሉ ሊሰሙት ወደ እርሱ ይቀርቡ ነበር።


ከማያምኑ ሰዎች አንዱ ቢጠራችሁ እናንተም ለመሄድ ብትፈልጉ ከሕሊና የተነሣ ሳትጠራጠሩ የሚያቀርቡላችሁን ሁሉ ብሉ።


በዚያም እራት አዘጋጁለት፤ ማርታም ታገለግል ነበር፤ አልዓዛር ግን ከእርሱ ጋር ከተቀመጡት መካከል አንዱ ነበረ።


በቤቱም በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ ብዙ ቀራጮችና ኀጢአተኞች ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ተቀመጡ፤ ብዙ ነበሩ፤ ይከተሉትም ነበር።


በቤቱም በማዕድ ተቀምጦ ሳለ፥ እነሆ፥ ብዙ ቀራጮችና ኃጢአተኞች መጥተው ከኢየሱስና ከደቀ መዛሙርቱ ጋር አብረው ተቀመጡ።


የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ሽልማት ታገኛላችሁ? ቀራጮች እንኳ ይህንኑ ያደርጉ የለምን?


ኢየሱስም ከዚያ አልፎ ሲሄድ ማቴዎስ የሚባል አንድ ሰው በቀረጥ መቀበያ ስፍራ ተቀምጦ አየውና “ተከተለኝ” አለው። ተነሥቶም ተከተለው።


የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ፤ እነርሱም ‘እነሆ በላተኛና ጠጪ፥ የቀራጮችና የኃጢአተኞች ወዳጅ’ አሉት። ጥበብ በሥራዋ ጸደቀች።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements