Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 4:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 ከምኵራብም ተነሥቶ ወደ ስምዖን ቤት ገባ። የስምዖንም አማት በብርቱ ትኩሳት ታማ ነበር፤ ስለ እርሷም ለመኑት።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ ከምኵራብ ወጥቶ ወደ ስምዖን ቤት ገባ። የስምዖንም ዐማት ኀይለኛ ትኵሳት ይዟት ታምማ ነበር፤ እንዲፈውሳትም ስለ እርሷ ለመኑት።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 ኢየሱስ ከምኲራብ ተነሥቶ ወደ ስምዖን ቤት ሄደ፤ እዚያም የስምዖን ዐማት በጣም አተኲሶአት ታማ ተኝታ ነበር፤ ስለዚህ እንዲያድናት ኢየሱስን ለመኑት።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 ከም​ኵ​ራ​ቡም ወጥቶ ወደ ስም​ዖን ቤት ገባ፤ የስ​ም​ዖን አማ​ትም በብ​ርቱ ንዳድ ታማ ነበ​ርና ስለ እር​ስዋ ነገ​ሩት።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 በምኵራብም ተነሥቶ ወደ ስምዖን ቤት ገባ። የስምዖንም አማት በብርቱ ንዳድ ታማ ነበር ስለ እርስዋም ለመኑት።

See the chapter Copy




ሉቃስ 4:38
9 Cross References  

አሁንም ከእግዚአብሔር የምትለምነውን ሁሉ እግዚአብሔር እንደሚሰጥህ አውቃለሁ፤” አለችው።


እንደ ሌሎቹ ሐዋርያትና እንደ ጌታ ወንድሞች እንደ ኬፋም፥ አማኝ ሚስታችንን ይዘን ልንዞር መብት የለንምን?


ስለዚህም እኅቶቹ “ጌታ ሆይ! እነሆ የምትወደው ታሞአል፤” ብለው ወደ እርሱ ላኩበት።


እርሱ ግን አንድ ቃልም አልመለሰላትም። ደቀ መዛሙርቱም ቀርበው “ከኋላችን እየጮኸች ነውና አሰናብታት” እያሉ ለመኑት።


ዝናው በመላዋ ሶርያ ሁሉ ተሰማ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይ ተይዘው የታመሙትን ሁሉ፥ አጋንንት ያደሩባቸውን፥ በጨረቃ የሚነሣባቸውንና ሽባዎችን ወደ እርሱ አመጡ፤ እርሱም ፈወሳቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements