Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 3:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እርሱም፦ “ከታዘዘላችሁ አብልጣችሁ ምንም አትሰብስቡ፤” አላቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እርሱም፣ “ከታዘዛችሁት በላይ ቀረጥ አትሰብስቡ” አላቸው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እርሱም፦ “በሕግ ከታዘዘላችሁ አብልጣችሁ አትጠይቁ፤” አላቸው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እር​ሱም፥ “ከታ​ዘ​ዛ​ች​ሁት አት​ር​ፋ​ችሁ አት​ው​ሰዱ” አላ​ቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 ከታዘዘላችሁ አብልጣችሁ አትውሰዱ አላቸው።

See the chapter Copy




ሉቃስ 3:13
15 Cross References  

ወይም ሌቦች ወይም ስግብግቦች ወይም ሰካራሞች ወይም ተሳዳቢዎች ወይም ነጣቂዎች የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም።


ዘኬዎስ ግን ቆሞ ጌታን “ጌታ ሆይ! ካለኝ ሁሉ እኩሌታውን ለድኾች እሰጣለሁ፤ ማንንም በሐሰት ከስሼ እንደሆንሁ አራት እጥፍ እመልሳለሁ፤” አለው።


የሰረቀ ከእንግዲህ ወዲህ አይስረቅ፤ ነገር ግን በዚያ ፈንታ ለጎደለው የሚያካፍለው እንዲኖረው በገዛ እጆቹ መልካምን እየሠራ ይድከም።


ሰው ሆይ፥ መልካም ምን እንደሆነ ለአንተ ነግሮሃል፤ ፍትሕን እንድታደርግ፥ ምሕረትን እንድትወድና ከአምላክህም ጋር በትሕትና እንድትሄድ ካልሆነ በቀር ጌታ ከአንተ የሚፈልገው ምንድነው?


እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ሕግና ነቢያትም ይህ ነውና።


እንግዲህ እነደዚህ ዓይነት ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ማንኛውንም ሸክምና የተጣበቅንበትን ኅጢአት ሁሉ አራግፈን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በጽናት እንሩጥ።


ጥፋቱን የሚሰውር አይለማም፥ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል።


ፍርዱ ሁሉ በፊቴ ነበረና፥ ሥርዓቱንም ከፊቴ አላራቅሁም።


ግብር ቀራጮችም ደግሞ ሊጠመቁ መጥተው፦ “መምህር ሆይ! ምን እናድርግ?” አሉት።


ወታደሮችም እንዲሁ፦ “እኛስ ምን እናድርግ?” ብለው ይጠይቁት ነበር። እርሱም፦ “ማንንም በግፍ ወይም በሐሰት ክስ አትበዝብዙ፤ ደመወዛችሁም ይብቃችሁ፤” አላቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements