Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 22:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 እርሱም “አሁን ግን ቦርሳ ያለው ይያዘው፤ ከረጢትም ያለው እንዲሁ፤ የሌለውም ልብሱን ሽጦ ሰይፍ ይግዛ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 እርሱም እንዲህ አላቸው፤ “አሁን ግን ኰረጆም፣ ከረጢትም ያለው ሰው ይያዝ፤ ሰይፍ የሌለውም ልብሱን ሽጦ ይግዛ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “አሁን ግን የገንዘብ ቦርሳም ሆነ ከረጢት ያለው ይያዝ፤ ሰይፍም የሌለው ልብሱን ሸጦ ሰይፍ ይግዛ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “አሁን ግን ኮሮጆ ያለው ኮሮ​ጆ​ውን ይያዝ፤ ከረ​ጢ​ትም ያለው እን​ዲሁ ያድ​ርግ፤ ሰይፍ የሌ​ለ​ውም ልብ​ሱን ሸጦ ሰይፍ ይግዛ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 እርሱም፦ አሁን ግን ኮረጆ ያለው ከእርሱ ጋር ይውሰድ፥ ከረጢትም ያለው እንዲሁ፤ የሌለውም ልብሱን ሽጦ ሰይፍ ይግዛ።

See the chapter Copy




ሉቃስ 22:36
10 Cross References  

በእውነት ከእናንተ ጋር ሳለን፥ መከራ እንደምንቀበል አስቀድመን እንነግራችሁ ነበር፤ እንዲሁም ደግሞ ሆነ፤ ይህንንም ታውቃላችሁ።


በእኔ ሳላችሁ ሰላም እንዲሆንላችሁ ይህን ተናግሬአችኋለሁ። በዓለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ፤ ነገር ግን አይዞአችሁ፤ እኔ ዓለምን አሸንፌዋለሁ፤”


እንግዲህ ክርስቶስ በሥጋ ስለ እኛ መከራን በመቀበሉ፥ እናንተም በዚህ ሐሳብ ራሳችሁን አስታጥቁ፤ ምክንያቱም በሥጋ መከራን የተቀበለ ኃጢአትን ትቶአል።


‘ባርያ ከጌታው አይበልጥም፤’ ብዬ የነገርኋችሁን ቃል አስቡ። እኔን ካሳደዱኝ እናንተን ደግሞ ያሳድዱአችኋል፤ ቃሌንም ከጠበቁ ቃላችሁን ደግሞ ይጠብቃሉ።


ለመንገዳችሁ ከረጢት ወይም ሁለት እጀ ጠባብ ወይም ጫማ ወይም በትር አትያዙ፤ ለሠራተኛ ምግቡ ይገባዋልና።


ከዚያም፥ “ያለ ቦርሳና ያለ ከረጢት፥ ያለ ጫማም በላክኋችሁ ጊዜ፥ የጐደለባችሁ ነገር ነበርን?” አላቸው። እነርሱም “ምንም” አሉ።


ይህ ‘ከዓመፀኞች ጋር ተቈጠረ፤’ ተብሎ የተጻፈው በእኔ ላይ የግድ መፈጸም አለበት እላችኋልለሁ፤ አዎን፤ ስለ እኔ የተባለው አሁን ይፈጸማልና፤” አላቸው።


እነርሱም “ጌታ ሆይ! እነሆ፥ በዚህ ሁለት ሰይፎች አሉ፤” አሉት። እርሱም “ይበቃል፤” አላቸው።


Follow us:

Advertisements


Advertisements