Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 22:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በእግዚአብሔር መንግሥት እስኪፈጸም ድረስ፥ ወደ ፊት ከዚህ አልበላም እላችኋለሁና፤” አላቸው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 እላችኋለሁ፤ በእግዚአብሔር መንግሥት የዚህ ትርጕም እስኪፈጸም ድረስ ይህን ፋሲካ ዳግመኛ አልበላም።”

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 የዚህ ነገር እውነተኛ ምሥጢር በእግዚአብሔር መንግሥት ፍጹም ሆኖ እስኪገለጥ ድረስ ከእንግዲህ ወዲህ ይህን የፋሲካ ራት ከቶ አልበላም እላችኋለሁ።”

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ነገር ግን፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥት እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ እን​ግ​ዲህ ከእ​ርሱ እን​ደ​ማ​ል​በላ እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ” አላ​ቸው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 እላችኋለሁና፥ በእግዚአብሔር መንግሥት እስኪፈጸም ድረስ፥ ወደ ፊት ከዚህ አልበላም አላቸው።

See the chapter Copy




ሉቃስ 22:16
11 Cross References  

መልአኩም “ወደ በጉ ሰርግ እራት የተጠሩ ብፁዓን ናቸው፤” ብለህ ጻፍ፤ አለኝ። ደግሞም “ይህ የእግዚአብሔር እውነተኛ ቃል ነው፤” አለኝ።


በማእድ ከተቀመጡትም አንዱ ይህን ሰምቶ “በእግዚአብሔር መንግሥት እንጀራ የሚበላ ብፁዕ ነው፤” አለው።


በመንግሥቴም ከእኔ ማዕድ ትበላላአችሁ፥ እንዲሁም ትጠጣላችሁ፤ በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ላይም ለመፍረድ በዙፋኖች ላይ ትቀመጣላችሁ።


ይኸውም ለሕዝብ ሁሉ አይደለም፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር አስቀድሞ የተመረጡ ምስክሮች ለሆንን ለእኛ ነው እንጂ፤ ከሙታንም ከተነሣ በኋላ ከእርሱ ጋር የበላን የጠጣንም እኛ ነን።


ለሚጠፋ መብል አትሥሩ፤ ነገር ግን የለዘለዓለም ሕይወት ለሚሆነው መብል ሥሩ፤ ይህም የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ነው፤ እርሱን እግዚአብሔር አብ አትሞታልና።”


ጌታቸው በመጣ ጊዜ ሲተጉ የሚያገኛቸው እነዚያ ባርያዎች ብፁዓን ናቸው፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ታጥቆ በማዕድ ያስቀምጣቸዋል፤ ቀርቦም ያገለግላቸዋል።


እርሱም “ከመከራዬ በፊት ይህን ፋሲካ ከእናንተ ጋር ልበላ እጅግ እመኝ ነበር፤


የእግዚአብሔር መንግሥት እስክትመጣ ድረስ ከአሁን ጀምሮ ከወይኑ ፍሬ አልጠጣም እላችኋለሁና” አለ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements