Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 2:38 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

38 በዚያችም ሰዓት ቀርባ እግዚአብሔርን አመሰገነች፤ የኢየሩሳሌምንም ቤዛ ለሚጠባበቁ ሁሉ ስለ እርሱ ትናገር ነበር።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

38 በዚያም ጊዜ ቀርባ እግዚአብሔርን አመሰገነች፤ የኢየሩሳሌምንም መቤዠት ለሚጠባበቁ ሁሉ ስለ ሕፃኑ ተናገረች።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

38 በዚያኑ ጊዜ እርስዋም መጥታ ጌታን ታመሰግን ጀመር፤ ስለ ሕፃኑም የኢየሩሳሌምን መዳን በተስፋ ለሚጠባበቁ ሁሉ ትናገር ነበር።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

38 ያን​ጊ​ዜም ተነ​ሥታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ሰ​ገ​ነች፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም ድኅ​ነት ተስፋ ለሚ​ያ​ደ​ርጉ ሁሉ ስለ እርሱ ተና​ገ​ረች።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

38 በዚያችም ሰዓት ቀርባ እግዚአብሔርን አመሰገነች፤ የኢየሩሳሌምንም ቤዛ ለሚጠባበቁ ሁሉ ስለ እርሱ ትናገር ነበር።

See the chapter Copy




ሉቃስ 2:38
11 Cross References  

እነሆም፥ በኢየሩሳሌም ስምዖን የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ ይህም ሰው የእስራኤልን መጽናናት የሚጠብቅ፥ ጻድቅና ትጉህም ነበረ፤ መንፈስ ቅዱስም በእርሱ ላይ ነበረ።


ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን።


እኛ ግን እስራኤልን የሚታደገው እርሱ ነው ብለን ተስፋ አድርገን ነበር፤ ሆኖም ይህ ነገር ከሆነ ሦስተኛው ቀን ነው።


“የእስራኤል ጌታ አምላክ ይባረክ፤ ጐብኝቶ ለሕዝቡ ቤዛ አድርጎአልና፤


በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ በሰማያዊ ስፍራ በክርስቶስ የባረከን፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይባረክ።


ይህም በምክራቸውና በሥራቸው አልተባበረም ነበር፤ አርማትያስም ከምትባል ከአይሁድ ከተማ ሆኖ እርሱ በበኩሉ የእግዚአብሔርን መንግሥት ይጠባበቅ ነበር።


የተከበረ የሸንጎ አባልና የእግዚአብሔርን መንግሥት ይጠባበቅ የነበረው የአርማትያሱ ዮሴፍ በድፍረት ወደ ጲላጦስ ሄዶ የኢየሱስን ሥጋ ለመነው።


ከአሴር ወገንም የሆነች የፋኑኤል ልጅ ሐና የምትባል አንዲት ነቢይት ነበረች፤ በዕድሜዋም በጣም የገፋች ነበረች፤ እርሷም ከድንግልናዋ ጀምራ ከባልዋ ጋር ሰባት ዓመት ኖረች፤


Follow us:

Advertisements


Advertisements