Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 19:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ‘ላለው ሁሉ ይሰጠዋል፤ ከሌለው ግን ያው ያለው ስንኳ ይወሰድበታል እላችኋለሁ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 “እርሱም እንዲህ አለ፤ ‘እላችኋለሁ፤ ላለው ይጨመርለታል፤ የሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ጌትዮውም ‘ላለው ሁሉ ይበልጥ ይሰጠዋል፤ ከሌለው ሰው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል እላችኋለሁ።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 እር​ሱም እን​ዲህ አላ​ቸው፦ ላለው ሁሉ ይሰ​ጡ​ታል፤ ይጨ​ም​ሩ​ለ​ታ​ልም፤ የሌ​ለ​ውን ግን ያን ያለ​ው​ንም ቢሆን ይወ​ስ​ዱ​በ​ታል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 እላችኋለሁ፥ ላለው ሁሉ ይሰጠዋል፥ ከሌለው ግን ያው ያለው ስንኳ ይወሰድበታል።

See the chapter Copy




ሉቃስ 19:26
17 Cross References  

የሠራችሁትን እንዳታጠፉ ነገር ግን ሙሉ ደመወዝን እንድትቀበሉ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።


ስለዚህ እንዴት እንደምትሰሙ በጥንቃቄ አጢኑ፤ ላለው ሁሉ ይሰጠዋልና፤ ከሌለውም ሁሉ፥ ያው ያለው የሚመስለው እንኳ ይወሰድበታል።”


ስለዚህ እላችኋለሁ፥ የእግዚአብሔር መንግሥት ከእናንተ ተወስዳ ፍሬዋን ለሚያፈራ ሕዝብ ትሰጣለች።


ላለው ይሰጠዋልና ይበዛለታልም፤ የሌለው ግን ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።


ላለው ይሰጠዋልና፤ ከሌለውም ያው ያለው እንኳ ይወሰድበታል።”


በትዕግስት መጽናትህንና ስለ ስሜ መከራ መቀበልህን አውቃለሁ።


ሳሙኤልም እንዲህ አለው፤ “ጌታ የእስራኤልን መንግሥት ዛሬ ከአንተ ቀዶታል፤ ከአንተም ለሚሻል ለጎረቤትህ አሳልፎ ሰጥቶታል።


ስለዚህ የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘በእውነት ቤትህ፥ የአባትህም ቤት ለዘለዓለም በፊቴ እንዲኖር ተናግሬአለሁ፤’ አሁን ግን ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ያከበሩኝን አከብራለሁና፥ የናቁኝም ይናቃሉና ይህ ከእኔ ይራቅ።


እነሆ ቶሎ ብዬ እመጣለሁ፤ ማንም አክሊልህን እንዳይወስድብህ ያለህን አጽንተህ ያዝ።


መጋቢውም በልቡ ‘ጌታዬ መጋቢነቱን ከእኔ ይወስዳልና ምን ላድርግ? ለመቈፈር ኃይል የለኝም፤ መለመንም አፍራለሁ።


ከአንተ በፊት ካስወገድሁት ከሳኦል ምሕረቴን እንዳራቅሁ ከእርሱ ግን አላርቅም።


በመዝሙር መጽሐፍ ‘መኖሪያው ምድረ በዳ ትሁን፤ የሚኖርባትም አይኑር፤’ ደግሞም ‘ሹመቱን ሌላ ይውሰዳት፤’ ተብሎ ተጽፎአልና።


ዘመኖቹም ጥቂት ይሁኑ፥ ሹመቱንም ሌላ ይውሰድ።


እነርሱም ‘ጌታ ሆይ! ዐሥር ምናን አለው፤’ አሉት።


Follow us:

Advertisements


Advertisements