Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 18:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

34 እነርሱም ከዚህ ነገር ምንም አላስተዋሉም፤ ይህም ንግግር ተሰውሮባቸው ነበር፤ የተናገረውንም አላወቁም።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

34 ደቀ መዛሙርቱ ግን ከዚህ ሁሉ የተረዱት አንድም ነገር አልነበረም፤ አባባሉም ተሰውሮባቸው ነበር፤ ስለ ምን እንደ ተናገረም አላወቁም።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

34 ደቀ መዛሙርቱ ግን ከዚህ ሁሉ ነገር አንዱንም አልተረዱም፤ የንግግሩም ምሥጢር ተሰውሮባቸው ስለ ነበር ምን ማለቱ እንደ ሆነ አላወቁም።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

34 እነ​ርሱ ግን፤ ከተ​ና​ገ​ራ​ቸው ያስ​ተ​ዋ​ሉት የለም፤ ይህ ነገር ከእ​ነ​ርሱ የተ​ሰ​ወረ ነበ​ርና፤ የተ​ና​ገ​ረ​ው​ንም አያ​ው​ቁም ነበ​ርና።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

34 እነርሱም ከዚህ ነገር ምንም አላስተዋሉም፥ ይህም ቃል ተሰውሮባቸው ነበር፥ የተናገረውንም አላወቁም።

See the chapter Copy




ሉቃስ 18:34
9 Cross References  

እነርሱ ግን ይህን ነገር አላስተዋሉም፤ እንዳይገባቸውም ተሰውሮባቸው ነበር፤ ስለዚህም ነገር እርሱን ለመጠየቅ ፈሩ።


እነርሱ ግን የሚላቸው አልገባቸውም፤ እንዳይጠይቁትም ፈሩ።


ደቀ መዛሙርቱም ይህን ነገር በመጀመሪያ አላስተዋሉም፤ ነገር ግን ኢየሱስ ከከበረ በኋላ በዚያን ጊዜ ይህ ስለ እርሱ እንደ ተጻፈ ይህንም እንዳደረጉለት ትዝ አላቸው።


ኢየሱስ ይህንን ምሳሌ ነገራቸው፤ እነርሱ ግን የነገራቸው ምን እንደሆነ አላስተዋሉም።


በዚያን ጊዜም መጻሕፍትን እንዲያስተውሉ አእምሮአቸውን ከፈተላቸው፤


እርሱም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ የማታስተውሉ፤ ነቢያትም የተናገሩትን ሁሉ ልባችሁ ከማመን የዘገየ፤


እነርሱም የተናገራቸውን ነገር አላስተዋሉም።


ከገረፉትም በኋላ ይገድሉታል፤ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል።”


Follow us:

Advertisements


Advertisements