Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 18:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታልና፤ ያፌዙበታልም፤ ያንገላቱትማል፤ ይተፉበትማል፤

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፤ እነርሱም ያፌዙበታል፤ ያንገላቱታል፤ ይተፉበታል፤ ይገርፉታል፤ ከዚያም ይገድሉታል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 እርሱ ለአሕዛብ ተላልፎ ይሰጣል፤ እነርሱም ያፌዙበታል፤ ይሰድቡታል፤ ይተፉበታል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 ለአ​ሕ​ዛብ አሳ​ል​ፈው ይሰ​ጡ​ታል፤ ይዘ​ብ​ቱ​በ​ታ​ልም፤ ይሰ​ድ​ቡ​ታ​ልም፤ ይተ​ፉ​በ​ታ​ልም።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታልና፥ ይዘብቱበትማል ያንገላቱትማል ይተፉበትማል፤

See the chapter Copy




ሉቃስ 18:32
26 Cross References  

ሄሮድስም ከሠራዊቱ ጋር ናቀው፤ አፌዘበትም፤ የጌጥ ልብስም አልብሶ ወደ ጲላጦስ መልሶ ላከው።


የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው፥ ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚያዞርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም።


ጀርባዬን ለገራፊዎች፥ ጉንጬንም ለጠጉር ነጪዎች ሰጠሁ፤ ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስሁም።


የአብርሀምና የይስሐቅ የያዕቆብም አምላክ፥ የአባቶቻችን አምላክ፥ እናንተ አሳልፋችሁ የሰጣችሁትንና ሊፈታው ቆርጦ ሳለ በጲላጦስ ፊት የካዳችሁትን ብላቴናውን ኢየሱስን አከበረው።


በዚህ ጊዜ አንዳንዶቹ ይተፉበት ጀመር፤ ዐይኑንም ሸፍነው በጡጫ እየመቱት፥ “እስቲ ትንቢት ተናገር” ይሉት ነበር። ሎሌዎችም በጥፊ እየመቱ ወሰዱት።


በዚያን ጊዜ ፊቱ ላይ ተፉበት፥ መቱት፥ በጥፊም መቱት


ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም መሄድ እንዳለበት ከሽማግሌዎች፥ ከካህናት አለቆችና ከጻፎች ብዙ መከራ እንደሚቀበልና እንደሚገደል በሦስተኛውም ቀን እንደሚነሣ ለደቀ መዛሙርቱ ይነግራቸው ጀመር።


አንቺ ግን ቤተልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትንሽ ነሽ፥ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘለዓለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።


ፊቱ ከሰዎች ሁሉ ይልቅ፥ መልኩም ከሰዎች ልጆች ይልቅ ተጐሳቁሎአልና ብዙ ሰዎች ስለ አንተ እንደ ተደነቁ፥ እንዲሁ ብዙ አሕዛብን ያስደንቃል፤


እርሱንም በእግዚአብሔር በተወሰነው አሳቡና በቀደመው እውቀቱ ተሰጥቶ በዐመፀኞች እጅ ሰቅላችሁ ገደላችሁት።


ጲላጦስ መልሶ “እኔ አይሁዳዊ ነኝን? ወገኖችህና የካህናት አለቆች ለእኔ አሳልፈው ሰጡህ፤ ምን አድርገሃል?” አለው።


እነርሱም መልሰው “ይህ ሰው ክፉ አድራጊ ባይሆን ለአንተ አሳልፈን ባልሰጠነውም ነበር” አሉት።


ይህንን ባለ ጊዜ በዚያ ቆመው ከነበሩት ሎሌዎች አንዱ “ለሊቀ ካህናቱ እንዲህ ትመልሳለህን?” ብሎ ኢየሱስን በጥፊ መታው።


ሕዝቡም ቆመው ይመለከቱ ነበር። መኰንኖቹም “ሌሎችን አዳነ፤ እርሱ በእግዚአብሔር የተመረጠው ክርስቶስ ከሆነ፥ ራሱን ያድን፤” እያሉ ያፌዙበት ነበር።


የተሰበሰቡት በሙሉ ተነሥተው ወደ ጲላጦስ ወሰዱትና


አስረውም ወሰዱት፤ ለገዢው ለጲላጦስ አሳልፈው ሰጡት።


ኢየሱስንም ከቀያፋ ወደ ገዢው ግቢ ወሰዱት፤ ማለዳም ነበረ፤ እነርሱም እንዳይረክሱ፥ ይልቁንም የፋሲካን በግ እንዲበሉ በማለት ወደ ገዢው ግቢ አልገቡም።


ጠዋት በማለዳ የካህናት አለቆች ከሽማግሌዎች፥ ከጸሓፍትና ከመላው የሸንጎ አባላት ጋር ወዲያው ከተማከሩ በኋላ ኢየሱስን አስረው ወሰዱት፤ ለጲላጦስም አሳልፈው ሰጡት።


እንዲያላግጡበት፥ እንዲገርፉትና እንዲሰቅሉት ለአሕዛብ አሳልፈው ይሰጡታል፤ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል።”


የቀሩትም ባርያዎቹን ይዘው ሰደቡአቸው፤ ገደሉአቸውም።


ከገረፉትም በኋላ ይገድሉታል፤ በሦስተኛውም ቀን ይነሣል።”


ይህም ኢየሱስ በምን ዓይነት ሞት እንደሚሞት ሲያመለክት የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ ነብር።


Follow us:

Advertisements


Advertisements