Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 16:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 በኋላም ሌላውን ‘አንተስ ስንት ዕዳ አለብህ?’ አለው። እርሱም ‘መቶ ዳውላ ስንዴ’ አለ። ‘የጽሑፍ ማስረጃህን እንካ ሰማንያ ብለህም ጻፍ፤’ አለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “ከዚያም ሌላውን፣ ‘አንተስ ስንት አለብህ?’ አለው። “እርሱም፣ ‘ዐምሳ ዳውላ ስንዴ’ አለው። “መጋቢውም፣ ‘የብድር ደብዳቤህን ዕንካ፤ “አርባ ዳውላ” ብለህ ጻፍ’ አለው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ሁለተኛውንም ጠርቶ፥ ‘የአንተስ ዕዳ ምን ያኽል ነው?’ አለው። እርሱም ‘መቶ ዳውላ ስንዴ ዕዳ አለብኝ’ ሲል መለሰ። መጋቢውም ‘ይኸው የፈረምከው ውል! ሰማኒያ ዳውላ ብለህ ጻፍ’ አለው።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም፦ ‘አን​ተሳ ለጌ​ታዬ የም​ት​ከ​ፍ​ለው ዕዳ ምን ያህል ነው?’ አለው፤ እር​ሱም፦ ‘መቶ ማድጋ ስንዴ ነው’ አለው፤ ‘እነሆ፥ ደብ​ዳ​ቤህ፤ ተቀ​ም​ጠህ ሰማ​ንያ አለ​ብኝ ብለህ ፈጥ​ነህ ጻፍ’ አለው።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 በኋላም ሌላውን፦ አንተስ ስንት ዕዳ አለብህ? አለው። እርሱም፦ መቶ ጫን ስንዴ አለ። ደብዳቤህን እንካ ሰማንያ ብለህም ጻፍ አለው።

See the chapter Copy




ሉቃስ 16:7
7 Cross References  

እንደገናም ሦስተኛውን ላከ፤ እነርሱም ይኸኛውን ደግሞ አቁሰለው አስወጡት።


ይህንንም ምሳሌ ለሕዝቡ ይነግራቸው ጀመር። “አንድ ሰው የወይን አትክልት ተከለ፤ ለወይን ጠባቂዎች አከራይቶ ለረጅም ጊዜ ወደ ሌላ አገር ሄደ።


ነገር ግን ያ ባርያ ከዚያ ወጥቶ መቶ ዲናር ዕዳ ያለበትን ከባልንጀሮቹ ባርያዎች አንዱን አገኘና ‘ዕዳህን ክፈለኝ’ ብሎ አንቆ ያዘው።


እርሷም እስከ ሰማኒያ አራት ዓመቷ ድረስ መበለት ነበረች፤ በጾምና በጸሎትም ሌሊትና ቀን እያገለገለች ከመቅደስ አትለይም ነበር።


እርሱም ‘መቶ ማድጋ ዘይት’ አለ። ‘የጽሑፍ ማስረጃህን እንካ፥ ፈጥነህም ተቀምጠና ኀምሳ ብለህ ጻፍ፤’ አለው።


ጌታውም ዐመፀኛውን መጋቢ ስለ ብልኃቱ አመሰገነው፤ የዚህ ዓለም ልጆች ለትውልዳቸው ከብርሃን ልጆች ይልቅ ብልኆች ናቸውና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements