Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 14:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 የጠራውንም ደግሞ እንዲህ አለው “ምሳ ወይም እራት ባሰናዳህ ጊዜ፥ ምናልባት እነርሱም በተራቸው እንዳይጠሩህ፥ እንዳይክሱህም፥ ወዳጆችህንና ወንድሞችህን ዘመዶችህንም ሀብታም ጎረቤቶችህንም አትጥራ።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ኢየሱስም የጋበዘውን ሰው ደግሞ እንዲህ አለው፤ “የምሳ ወይም የእራት ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ፣ በዐጸፋው እንዳይጋብዙህና ብድራትን እንዳይመልሱልህ፣ ወዳጆችህን ወይም ወንድሞችህን ወይም ዘመዶችህን ወይም ከበርቴ ጎረቤቶችህን አትጋብዝ።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ኢየሱስ ጋባዡን ሰው ደግሞ እንዲህ አለው፦ “የምሳ ወይም የእራት ግብዣ በምታደርግበት ጊዜ ብድራቸውን ለመመለስ በተራቸው የሚጋብዙህን ወዳጆችህን፥ ወንድሞችህን፥ ዘመዶችህን፥ ሀብታሞች ጐረቤቶችህንም አትጥራ፤

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 የጠ​ራ​ው​ንም እን​ዲህ አለው፥ “በበ​ዓል ምሳ ወይም ራት በም​ታ​ደ​ር​ግ​በት ጊዜ ወዳ​ጆ​ች​ህ​ንና ወን​ድ​ሞ​ች​ህን፥ ዘመ​ዶ​ች​ህ​ንና ጎረ​ቤ​ቶ​ች​ህን፥ ባለ​ጸ​ጎች ባል​ን​ጀ​ሮ​ች​ህ​ንም አት​ጥራ፤ እነ​ር​ሱም ይጠ​ሩ​ሃ​ልና፤ ብድ​ርም ይሆ​ን​ብ​ሃ​ልና።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 የጠራውንም ደግሞ እንዲህ አለው፦ ምሳ ወይም እራት ባደረግህ ጊዜ፥ እነርሱ ደግሞ በተራቸው ምናልባት እንዳይጠሩህ ብድራትም እንዳይመልሱልህ፥ ወዳጆችህንና ወንድሞችህን ዘመዶችህንም ባለ ጠጎች ጎረቤቶችህንም አትጥራ።

See the chapter Copy




ሉቃስ 14:12
13 Cross References  

የሚወዱአችሁን ብትወዱ ምን ሽልማት ታገኛላችሁ? ቀራጮች እንኳ ይህንኑ ያደርጉ የለምን?


ለራሱ ጥቅም ሲል ድሀን የሚጐዳ፥ ለሀብታም የሚሰጥ፥ እርሱ ወደ ድህነት ይወድቃል።


ድሀ በባልንጀራው ዘንድ የተጠላ ነው፥ የሀብታም ወዳጆች ግን ብዙዎች ናቸው።


የተራቡትን በበጎ ነገር አጥግቦአል፤ ሀብታሞችን ባዶአቸውን ሰዶአቸዋል።


ጎረቤቶችዋም ዘመዶችዋም ጌታ ታላቅ ምሕረቱን እንዳደረገላት ሰምተው ከእርሷ ጋር ደስ አላቸው።


ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፤ ራሱንም የሚያዋርድ ከፍ ይላል።”


ነገር ግን ግብዣ ባሰናዳህ ጊዜ ድሆችንና ጉንድሾችን አንካሶችንም ዐይነ ስውሮችንም ጥራ፤


ልጆቼ እንደ መሆናችሁ ግን ይህን እላችኋለሁ፤ እናንተም ደግሞ ልባችሁን ወለል አድርጋችሁ ክፈቱልን።


Follow us:

Advertisements


Advertisements