Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 12:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ቁራዎችን ተመልከቱ፤ አይዘሩም፤ አያጭዱምም፤ ዕቃ ቤትም ወይም ጎተራ የላቸውም፤ እግዚአብሔርም ይመግባቸዋል፤ እናንተማ ከወፎች እጅግ ትበልጡ የለምን?

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ቍራዎችን ተመልከቱ፤ አይዘሩም፤ አያጭዱም፤ ማከማቻ ወይም ጐተራ የላቸውም፤ እግዚአብሔር ግን ይመግባቸዋል። እናንተማ ከወፎች እጅግ ትበልጡ የለምን?

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 እስቲ ቊራዎችን ተመልከቱ! እነርሱ አይዘሩም ወይም አያጭዱም፤ የእህል ማከማቻ ቦታ ወይም ጐተራ የላቸውም፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ይመግባቸዋል፤ እናንተማ ከወፎች የቱን ያኽል ትበልጣላችሁ!

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 የማ​ይ​ዘ​ሩ​ት​ንና የማ​ያ​ጭ​ዱ​ትን፥ ጎተ​ራና ጕድ​ጓድ የሌ​ላ​ቸ​ውን የቍ​ራ​ዎ​ችን ጫጭ​ቶች ተመ​ል​ከቱ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ይመ​ግ​ባ​ቸ​ዋል፤ እን​ግ​ዲህ እና​ንተ ከወ​ፎች እን​ዴት እጅግ አት​በ​ል​ጡም?

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ቍራዎችን ተመልከቱ፤ አይዘሩም አያጭዱምም፥ ዕቃ ቤትም ወይም ጎተራ የላቸውም፥ እግዚአብሔርም ይመግባቸዋል፤ እናንተስ ከወፎች እንዴት ትበልጣላችሁ?

See the chapter Copy




ሉቃስ 12:24
13 Cross References  

ስለዚህ አትፍሩ ከብዙ ድንቢጦች ይልቅ እናንተ ትበልጣላችሁ።


ለእንስሶችም ምግባቸውን ይሰጣል ለሚጠሩት ለቁራዎች ጫጩቶችም እንዲሁ።


ነገር ግን የእናንተ የራሳችሁ ጠጉር ሁሉ እንኳ የተቆጠረ ነው፤ አትፍሩ፤ እናንተ ከብዙ ድንቢጦች ትበልጣላችሁ።


ልጆቹ ወደ እግዚአብሔር ሲጮኹ የሚበሉትም አጥተው ሲቅበዘበዙ፥ ለቁራ መብልን የሚሰጠው ማን ነው?”


ንጉሡ በነገሩ እጅግ አዘነ፤ በተጋበዙት እንግዶች ፊት የመሐላ ቃሉን ለማጠፍ አልፈለገም።


መንሹ በእጁ ነው፤ አውድማውንም ያጠራል፤ ስንዴውን በጎተራ ይከተዋል፥ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”


ወደ ሰማይ ወፎች ተመልከቱ፤ አይዘሩም፥ ወይም አያጭዱም፥ ወደ ጎተራም አይሰበስቡም፤ ነገር ግን የሰማዩ አባታችሁ ይመግባቸዋል፤ ታዲያ እናንተ ከእነርሱ እጅግ አትበልጡምን?


‘እንዲህ አደርጋለሁ፤ ጎተራዬን አፍርሼ ሌላ የሚበልጥ እሠራለሁ፤ በዚያም ፍሬዬንና በረከቴን ሁሉ አከማቻለሁ፤


ነፍስ ከመብል ሰውነትም ከልብስ ይበልጣልና።


Follow us:

Advertisements


Advertisements