Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ሉቃስ 11:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ከእርሱ ይልቅ የሚበረታ አደጋ ጥሎበት ካሸነፈው ግን፥ ታምኖበት የነበረውን የጦር ዕውቃን ይወስድበታል፤ ምርኮውንም ያካፍላል።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ነገር ግን ይበልጥ ብርቱ የሆነ ሰው መጥቶ ካጠቃውና ካሸነፈው ታምኖበት የነበረውን ትጥቁን ያስፈታዋል፤ ምርኮውንም ወስዶ ለሌሎች ያካፍላል።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ነገር ግን ከእርሱ የበለጠ ኀይለኛ ሰው መጥቶ ካሸነፈው የተማመነበትን የጦር መሣሪያ ይወስድበታል ንብረቱንም ሁሉ ዘርፎ ያካፍላል።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ከእ​ርሱ የሚ​በ​ረ​ታው ቢመ​ጣና ቢያ​ሸ​ን​ፈው ግን፥ ይታ​መ​ን​በት የነ​በ​ረ​ውን የጦር መሣ​ሪ​ያ​ውን ይገ​ፈ​ዋል፤ የማ​ረ​ከ​ው​ንና የዘ​ረ​ፈ​ውን ገን​ዘ​ቡ​ንም ይወ​ስ​ዳል።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ከእርሱ ይልቅ የሚበረታ ወጥቶ ሲያሸንፈው ግን፥ ታምኖበት የነበረውን ጋሻና ጦር ይወስድበታል ምርኮውንም ያካፍላል።

See the chapter Copy




ሉቃስ 11:22
14 Cross References  

ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአል፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአል፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።


በዚያም ቀን ጌታ ፈጣኑን እባብ ሌዋታንን፥ የሚጠቀለለውንም እባብ ሌዋታንን፥ በጠንካራ በታላቅ፥ በብርቱም ሰይፍ ይቀጣል፤ በባሕርም ውስጥ ያለውን ዘንዶ ይገድላል።


“በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ “በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፥ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፥ አንተም ሰኰናውን ትነድፋለህ።”


ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ፥ አሸንፋችኋቸዋልም፥ በእናንተ ያለው በዓለም ካለው ይበልጣልና።


ኃጢአትን የሚያደርግ ከዲያብሎስ ነው፥ ምክንያቱም ዲያብሎስ ከመጀመሪያ ጀምሮ ኃጢአትን ይሠራል። የእግዚአብሔር ልጅ የተገለጠውም የዲያብሎስን ሥራ ለማፍረስ ነው።


አለቅነትንና ሥልጣናትን ገፎ፥ በመስቀሉ ድል በመንሣት እነርሱን በይፋ አጋለጣቸው።


ጠላትም፦ አሳድጄ እይዛቸዋለሁ፥ ምርኮም እካፈላለሁ፥ በእነርሱም ፍላጎቴ ይሞላል፥ ሰይፌንም እመዝዛለሁ፥ እጄም ታጠፋቸዋለች አለ።


በማናቸውም ጊዜ ኀይለኛ ሰው በሚገባ የጦር ዕቃውን ታጥቆ የራሱን ግቢ ቢጠብቅ፥ ያለው ንብረቱ በሰላም የተጠበቀ ይሆናል፤


ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል፤ ከእኔ ጋርም የማይሰበስብ ይበትናል።


የዲያብሎስን ሽንገላ ለመቃወም እንድትችሉ፥ የእግዚአብሔርን ሙሉ የጦር ትጥቅ ልበሱ።


ስለዚህ በክፉው ቀን ለመቃወም፥ ሁሉንም ፈጽማችሁ ለመቆም እንድትችሉ የእግዚአብሔርን የጦር ትጥቅ አንሡ።


Follow us:

Advertisements


Advertisements