ሉቃስ 11:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 ሰይጣንም ደግሞ እርስ በርሱ ቢለያይ መንግሥቱ እንዴት ይቆማል? እኔ አጋንንትን በብዔልዜቡል እንደማወጣ እናንተ ብላችኋልና፤ See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 ሰይጣንም እርስ በርሱ ከተከፋፈለ፣ መንግሥቱ እንዴት ይጸናል? አጋንንትን በብዔልዜቡል እንደማወጣ ትናገራላችሁና። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 ስለዚህ ሰይጣን እርስ በርሱ የሚለያይ ከሆነ የእርሱ መንግሥት እንዴት ጸንቶ መቆም ይችላል? እናንተ ግን ‘እርሱ አጋንንትን የሚያስወጣ በብዔልዜቡል ነው፤’ ትሉኛላችሁ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 ሰይጣንስ እርስ በርሱ ከተለያየ መንግሥቱ እንዴት ይጸናል? በአጋንንት አለቃ በብዔል ዜቡል አጋንንትን ያወጣል ትላላችሁና። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 እኔ አጋንንትን በብዔል ዜቡል እንዳወጣ ትላላችሁና ሰይጣን ደግሞ እርስ በርሱ ከተለያየ መንግሥቱ እንዴት ትቆማለች? See the chapter |