Biblia Todo Logo
Online Bible

- Advertisements -




ዘሌዋውያን 8:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ከዚያም በኋላ ለጌታ በእሳት የሚቀርብ ቁርባን፥ መዓዛው ያማረ ሽታ የሆነ፥ የቅድስና መሥዋዕት አድርጎ ሙሴ ከእጃቸው ተቀብሎ በሚቃጥለው መሥዋዕት ላይ በመሠዊያው አቃጠለው።

See the chapter Copy

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ሙሴም ከእጃቸው ተቀብሎ፣ ለእግዚአብሔር በእሳት የሚቀርብ፣ መዐዛውም ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት አድርጎ በመሠዊያው ላይ በሚቃጠለው መሥዋዕት ላይ አቃጠለው።

See the chapter Copy

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ከዚህ በኋላ ሙሴ ምግቡን ከእነርሱ ወሰደ፤ ስለ ክህነት ሹመት መባ እንዲሆን በሚቃጠል መሥዋዕት መሠዊያ ላይ አድርጎ አቃጠለው፤ ይህም መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የምግብ ቊርባን ነበር።

See the chapter Copy

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

28 ሙሴም ከእ​ጃ​ቸው ተቀ​ብሎ በመ​ሠ​ዊ​ያው በሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ላይ አኖ​ረው። በጎ መዓዛ የቅ​ድ​ስና መሥ​ዋ​ዕት ነበረ። እር​ሱም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ሳት ቍር​ባን ነበረ።

See the chapter Copy

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

28 ሙሴም ከእጃቸው ተቀብሎ በመሠዊያው በሚቃጥለው መሥዋዕት ላይ አቃጠለው፤ የጣፋጭ ሽታ መቀደሻ ነበረ። እርሱም ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን ነበረ።

See the chapter Copy




ዘሌዋውያን 8:28
6 Cross References  

ከእጃቸውም ትቀበለዋለህ፥ በጌታ ፊት መልካም መዓዛ እንዲሆን በመሠዊያው ላይ ከሚቃጠል መሥዋዕት ጋር ታቃጥለዋለህ፤ ይህም ለጌታ የእሳት ቁርባን ነው።


ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፤ በጎቹም እንዲበተኑ እረኛውን ምታ፤ እጄንም በታናናሾች ላይ አዞራለሁ።


የመሥዋዕቱም መዓዛ ጌታን ደስ አሰኘው፤ ጌታም በሐሳቡ እንዲህ አለ፥ “ገና ከታናሽነቱ ጊዜ ጀምሮ የሰው ሐሳብ ክፉ ነውና፥ ሰው በሚፈጽመው በደል ምክንያት ከእንግዲህ ወዲህ ምድርን አልረግምም፤ አሁን እንዳደረግሁት ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አላጠፋም።


የሆድ ዕቃውንና እግሮቹን ግን በውኃ ያጥባል፤ ካህኑም የሚቃጠል መሥዋዕት፥ በእሳትም የሚቀርብ ቁርባን አድርጎ፥ በጌታ ዘንድ መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን ሁሉንም በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል።


Follow us:

Advertisements


Advertisements