ዘሌዋውያን 7:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)30 የእርሱ እጆች ለጌታ በእሳት የሚቀርበውን ቁርባን ያመጣሉ፤ እርሱም ፍርምባው በጌታ ፊት ለመወዝወዝ ቁርባን እንዲወዘወዝ ፍርምባውን ከስቡ ጋር ያመጣዋል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም30 በእሳት ለእግዚአብሔር የሚቀርበውን መሥዋዕት በራሱ እጅ ያቅርበው፤ ሥቡን ከፍርምባው ጋራ ያቅርብ፤ ፍርምባውን መሥዋዕት አድርጎ በእግዚአብሔር ፊት ይወዝውዘው። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም30 እርሱንም የሚቃጠል መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ያቅርብ፤ የእንስሳውንም ስብ ከፍርምባው ጋር በመወዝወዝ ለእግዚአብሔር ልዩ መባ አድርጎ ያቅርብ። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)30 የእርሱ እጆች ለእግዚአብሔር የእሳቱን ቍርባን ያመጣሉ፤ ፍርምባውን በእግዚአብሔር ፊት ቍርባን ያቀርብ ዘንድ በጉበቱ ላይ ያለውን መረብና የፍርምባውን ስብ ያመጣል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)30 የእርሱ እጆች ለእግዚአብሔር የእሳቱን ቁርባን ያመጣሉ፤ ፍርምባው በእግዚአብሔር ፊት ለመወዝወዝ ቁርባን ይወዘውዝ ዘንድ ስቡንና ፍርምባውን ያመጣል። See the chapter |