ዘሌዋውያን 7:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)18 በሦስተኛው ቀን ከአንድነቱ መሥዋዕት ከቶ ሥጋ ቢበላ፥ አይሠምርለትም ላቀረበው ሰው የተጠላ ይሆንበታል እንጂ ቁርባን ሆኖ አይቈጠርለትም፤ ሰውም ከእርሱ ቢበላ ኃጢአቱን ይሸከማል። See the chapterአዲሱ መደበኛ ትርጒም18 ማንኛውም የኅብረት መሥዋዕት ሥጋ በሦስተኛው ቀን ከተበላ ተቀባይነት የለውም፤ ርኩስ በመሆኑ ላቀረበው ሰው ዋጋ አይኖረውም፤ ከዚያም የበላ ሰው የበደል ዕዳ ይሆንበታል። See the chapterአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም18 ከተረፈው ሥጋ ምንም ያኽል በሦስተኛው ቀን ቢበላ የዚያን ሰው መሥዋዕት እግዚአብሔር አይቀበልለትም፤ መሥዋዕቱም እንደ ቀረበ ሆኖ አይቈጠርለትም፤ እንዲያውም እንደ ረከሰ ሆኖ ይቈጠራል፤ እርሱንም የበላ ሰው የበደሉን ፍዳ ይቀበላል። See the chapterየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)18 በሦስተኛው ቀን ከደኅንነት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ፥ አይሠምርም፤ ላቀረበው ሰው የተጠላ ይሆንበታል እንጂ ቍርባን ሆኖ አይቈጠርለትም፤ ከእርሱም የበላ ሰው ኀጢአቱን ይሸከማል። See the chapterመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)18 በሦስተኛው ቀን ከደኅንነት መሥዋዕት ሥጋ ቢበላ፥ አይሠምርም ላቀረበው ሰው የተጠላ ይሆንበታል እንጂ ቁርባን ሆኖ አይቈጠርለትም፤ ከእርሱም ቢበላ ኃጢአቱን ይሸከማል። See the chapter |